መዝገብ

Category: ርዕስ አንቀፅ

መንግሥት ሕግን ያክብር ከአዙሪት እንውጣ!!

በአንድ አገር ውስጥ ሕግን አክብሮ የሚኖር ሕዝብ ሕግን በሚያስከብር መንግስት ተከብሮ እንደሚኖር እና ሕግም ለአገረ መንግስት መዝለቅ እና መቃናት ዘብ ሆኖ ይቆማል። በአንድ አገርም ሕግን ከማክበር እና ከማስከበር አኳያ እከሌ እና እከሌ ተብሎ የማይለይ እና ሁሉም በሚኖርበት አገር ሕግ ተገዝቶ…

ከሁሉ በፊት ሕግ ይከበር!

በአንድ አገር ውስጥ መንግስት አቋም እና አገረ መንግስት ጥንካሬ በዋናነት የሚለካው መንግስት በአገር ውስጥ ሕግ እና ስርኣትን አስከብሮ ዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ ሲችል እንደሆነ በርካቶች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ይህም ታዲያ ዜጎች ሰርተው ግብርን በአግባቡ ለአገር ልማት፣ ዕድገት እንዲሁም ወረድ ሲልም ለራሳቸው…

የአዲስ ማለዳ የአንድ መቶ ሳምንታት ጉዞ!

የዛሬዋ አዲስ ማለዳ ለአንድ መቶኛ ዕትም መድረስ ያን ያክል ባያኩራራም ያስደስታል! ደስታው ለምን ቢሉ ያለማቋረጥ እዚህ ላይ መድረስ በቀላሉ አይቻልምና የሚል ምላሽ አለው። በሌላ በኩል ደግሞ አብረዋት፣ ወይም ቀደም ብለው አሊያም ዘግየት ብለው የጀመሩ ጋዜጦች በሚያሳዝን መልኩ መንገድ ላይ መቅረታቸውም…

የብር ቅየራው በትኩረት ቢጤን መልካም ነው

የገንዘብ ቅየራው የተለያዩ ስያሜዎች እና ትርጓሜዎች እየተሰጡት የተጀመረውን ጉዳይ ከዳር እንዲደርስም በተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት አማካኝነት ዕርዳታ እየተደረገለት እና የማስፈጸም ስራም እየተሰራ ይገኛል። ከወጣበት ገንዘብ አንጻር እና ከታቀደለት አላማ አንጻርም ጉዳዩ በሚገባ እንዲተገበርም እና በአፈጻጸምም በኩል እንዲሰምር የአገር ሀብት ነው…

ኃላፊነት ይመዘን!!

ከሰሞኑ አንድ ድንገተኛ የመንግስት ውሳኔ ተሰምቶ በርካታ ሩጫዎች የተስተዋሉባቸውን ጉዳዮች መመልከት እና ተቀዛቅዞ ነበረው ወይም ተዳፍኖ ነበረው የሕገ ወጥ ገንዘቦች ዝውውርም በይፋ በቁጥጥር ስር ሲውል ሰንብቷል። በቅርቡ ገንዘብ ቅየራው ጉድ ታዲያ በኢትዮያ በባንክ ስርዓት ውስጥ ከሚንቀሳቀሰው ይልቅ በኢመደበኛው የንግድ ስርዓት…

አዲሱ ዘመን ከባለፈው ውጥንቅጥ የምንላቀቅበት ሊሆን ይገባል!

2012 በዓለምም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች በርትተው የታዩበት ዓመት ሆኖ አልፏል። ችግሮቹ ከመበርታታቸውም የተነሳ የጥንታዊው የማያዊያን የዘመን አቆጣጠር በ2012 ላይ ማለቁ የዓለም መጨረሻን ያመላክታል የሚለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር እውን ሳይሆን ስላለፈ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ሊሆን…

ዝምታ ምላሽ አይሆንም!

ኹለት ዓመት ተኩልን እንደ ቀልድ ፉት ያለው የለውጡ መንግስት አዲሱ ኃይል ከመባል ይልቅ ወደ ለውጡ ኃይል መባል ስያሜ ለመለወጥ አፍታ አልገጀበትም። ይኸው ኃይል ታዲያ ወደ መንበር በመጣበት በመጀመሪ ቀናት ላይ በርካታ ቃል የገባቸውን እና ሊያከናውናቸው እነሆ በደጅ ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች…

ታሪክ ከፖለቲከኞች የግል መሣሪያነት ወደ ሕዝብ እጅ ሊገባ ይገባል!

ታሪክ የኋላውን ማስታወሻ፣ የዛሬን መወሰኛ እና የነገን ማቀጃ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። እንኳን በአገር ደረጃና በግለሰብም ቢሆን አንድ ሰው ትላንት ያሳለፈውና የቀደመ ልምዱ ለዛሬና ለነገ ግብዓት አድርጎ እንዲጠቀምበት፣ ከተሳሳተ እንዲማርበት፣ ጠንካራ ከነበረ ደግሞ በዛው እንዲገፋበት ይጠበቃል። የኢትዮጵያን የታሪክ ነገር በወፍ በረር…

ሹመኞች በተመደቡበት ስፍራ ይሰንብቱ!!

ካለፉት ኹለት ዓመት ተኩል ጀምሮ ለውጥ ንፋስ የምትተነፍሰው ኢትዮጵያ በርካታ አብይ ጉዳዮች ሲሰሙባት እና ሲታዩባት ውላ የምታድር አገር ከሆነች ዋል አደር ብላለች። ከጸጥታ ችግሮች፣ ከፖለቲካዊ ውጥንቅጥ እና መሰል ጉዳዮች ባለፈ የሚንስትሮች እና ካቢኔዎች ሹም ሽር እና በአንድ ስፍራ ረግቶ ያለመቆየት…

‹ተናጋሪዎች› ዝም በሉ፤ ዝም ያላችሁ ተናገሩ

ተቋማትን ለመገንባት እና ጠንካራ አገረ መንግስትን ለማቆም በሚል መልካም በሚመስል ግን ደግሞ ገደብ ባልተበጀለት አካሔድ በርካታ ጥፋቶች ሲሰነዘሩ እና በንጹሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ዕልቂት ሲካሔድ መታዘብ የዕለት ተዕለት ድርጊት ከሆነ ዋል አደር ብሏል። በእርግጥ በለውጥ ንፋስ ተገፍቶ አገር ከጭቆና…

መንግሥት የጥቃቱን ብሔር እና ኃይማኖት ተኮርነት በግልጽ ሊያምን ይገባል!

ባለፉት ኹለት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ያለመረጋጋት እና ግጭት ተስተውሏል። የተለየ ሰላማዊ የሚባል ክልል በሌለበት ሁኔታ በክልሎች ውስጥ አናሳ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች አባላት ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እንዲሁም ንብረታቸው ሲወድም ታይቷል። የእነዚህ ግጭቶች መነሻም ፖለቲካዊ፣ ኃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ታሪካዊ እየተደረገ ቢቀርብም በዋነኛነት…

የፍርድ ሒደቱን በማፋጠን መተማመንን እንገንባ!

በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በአንድም በሌላም ምክንያት ወደ ፍትህ ተቋማት ጎራ ብሎ ተገቢውን ግልጋሎት በማግኘት ረክቶ የተመለሰን ሰው ማግኘት እጅግ ከሚከብዱ የዓለማችን ስራዎች አንዱ ወደ መሆን እየተጠጋ እንደሆነ መታዘብ ይቻላል። ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በእስር እና በፍርድ ቤት ከክርክር ሒደት…

ኹከቱ ወረርሽኙን እንዳያስረሳን !

ካለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ አብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች፣ መዲናዋ አዲስ አበባ እንዲሁም ኢትዮጵያ እንደ አገር ውጥንቅጥ ውስጥ የገባችበት ጊዜ እንደነበር ኹሉም የሚታዘበው እና የሚያየው ጉዳይ ነው። ከድምጻዊ ሀጫሉ ግድያ ጋር የተያያዙ ግን ደግሞ ለመፈንዳት ጊዜን ሲጠብቁ ነበሩ በሚመስል አኳኋን በአንድ…

ሕግ ለማስከበር ሕግ ሲጣስ፤ ሕዝብስ?

የሰው ልጅ ከጅማሬው ጀምሮ በማኅበረሰባዊ ጎኑ እየጎለበት እስከ መጣበት እና አሁን ደግሞ ወደ ቀደመው ብቸኝነት ሕይወት መመለስ እስከ ጀመረበት ጊዜ ድረስ በርካታ ጉዳዮችን ፈጥሮ አጎልብቷል። በጥንታዊው ሰው የተጀመሩት እና ሰውን ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ከፍ በማድረግ የዝግመት ዕድገቱን ካፋጠኑት አንዱ…

ንዑስ ብሔርተኝነትን ማክረር ልጓም ሊበጅለት ይገባል!

በሕውሓት የሚመራው የኢሕአዴግ ጦር ግንቦት 20 1983 ደርግን ከሥልጣን አስወግዶ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ አገራዊ ብሔርተኝነት እየደበዘዘ ሔዶ በንዑስ ብሔርተኝነት በሰፊው ተተክቷል፡፡ ከባለፉት ኹለት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ በኩራት መናገር ለአደጋ የሚያጋልጥ ነበር፡፡ ለውጡ እንደመጣ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ…

መንግሥት የሕዝብ ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን ይወጣ!

ሰኞ፣ ሰኔ 22 ምሽት ሦስት ሰዓት ተኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ገላን ኮንዶሚኒየም በሚባለው ሰፈር ባታወቁ ሰዎች የተገደለውን ታዋቂውን የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ አሟሟት ተከትሎ በመዲናችን አዲስ አበባ እና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች እና ወረዳዎች ላይ ኹከት…

የመሬት ወረራን ሳይቃጠል በቅጠል

ባለፉት ዓመታት በተለይም ከኹለት ዓመታት ወዲህ እየታዩ ግን ደግሞ የዕርምት እርምጃዎችም ከመወሰድ የተቆጠቡባቸው ሕገ ወጥ ተግባራት መኖራቸውን በርካቶቻችን የምንስማማበት ጉዳይ ነው። በየቤታችን፣ መኖሪያችን አካባቢ፣ በመስሪያ ቤቶቻችን ዙሪያ እና በዕለት ተዕለት ከምንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች እነዚህ ሕገ ወጥ ናቸው የሚባሉ ግን በአደባባይ እየተከወኑ…

መጠንከር አሁን ነው!

ገና ከትልሙ ጀምሮ በኋላም ላይ ወደ መሬት ወርዶ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ከዛሬ ዘጠኝ ዓመታት በፊት ጀምሮ ሳንካ ያላጣው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አሁን ደግሞ ነገሮች እየተካረሩ በተለይም ደግሞ ከግብጽ በኩል እጅግ የበረታ ተቃውሞው እየቀረበ ይገኛል። ይህም ደግሞ ግብጽ ከዘመናት በፊት ጀምሮ…

ማኅበራዊ እሴቶች ሲናዱ መንግሥት ቆሞ እያየ ነው!

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በእጅጉ እየናረ መምጣት ከጀመረበት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ እና የ21ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ ትርፍን ከሁሉም ነገር በላይ በማስቀደም የሚታወቀው የካፒታሊዝም ስርዓት ያለ ተገዳዳሪ እየናኘ መጥቷል። በዚህም የተነሳ አገሮች በኀያላኑ ተጽዕኖ ሥር በመውደቅ ወደዱም ጠሉም ይህንን መንገድ እንዲከተሉ…

የሴቶች እና የሕፃናት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን መከላከል ትኩረት ይሰጠው!

ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ የሰው ዘርን በቀጥታ በማጥቃት እስካሁን ድረስ የ400 ሺህ ያህል ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉትን አጥቅቷል። በኢትዮጵያም እንዲሁ ወረርሽኙ የሰዎች ሕይወትን መቅጠፍ የጀመረ ሲሆን ሺዎችን የቫይረሱ ተጠቂ አድርጓል። በተለይ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ…

ወረርሽኙን ለመቋቋም የተሰባሰበውን እርዳታ ጥቅም ላይ ማዋል ሊጀመር ይገባል!

አዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ መናኸሪያ መሆኗ በዚህ ሳምንት ከመቼውም ይልቅ በጉልህ ተለይቷል። በአገሪቷ እስከ ከትናንት ወዲያ (ሐሙስ ግንቦት 20/2012) ከተያዙት 831 ሰዎች ውስጥ 552 ያህሉ ከአዲስ አበባ ናቸው። ከተማዋ የአገሪቱ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ መዲና መሆኗ ዓለም ዐቀፍ እንቅስቃሴዎች…

‹‹ብልህ ከሞኝ ውድቀት ይማራል››

በበርካታ የዓለም አገራት የወራት ዕድሜ ቢያስቆጥርም ቅሉ በርካቶችን ሕይወት በአጭር አስቀርቶ ያለፈው እና አሁንም ከባድ ጉዳት እያደረሰ ሚገኘው ኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ስጋት ከሆነ ዋል አደር ብሏል። ይህንም ተከትሎ በበርካታ አገራት ከቅድመጥንቃቄ ጉድለትም ሆነ ከፍተኛ ጥደንቃቄ ባደረጉት ላይ በሚፈጠር አነስተኛ…

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ ሰብዓዊ መብትን መጣስ ይቁም!

በዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአገራችን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊጣል እንደሚገባ ብዙዎች ቀድመው ሲወተውቱ ነበር፡፡ አዲስ ማለዳም ይህንን ሀሳብ ቀድመው ከደገፉ ወገኖች ውስጥ ነች፡፡ አዋጁ በባህሪው የሰብዓዊ መብቶችን የሚጥስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተረጋጋ ሁኔታ ባለበት ጊዜ የማይደረጉ ነገሮች በአስቸኳይ ጊዜ…

የለይቶ ማቆያዎች ጥበቃ ይጠናከር!

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ተሰራጭቶ እና ወረርሽኝነቱ ተረጋግጦ አገራት የተቻላቸውን የመከላከል እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል። በተለይም ደግሞ የወረርሽኙ መነሻ የሆነችው ቻይና አጣዳፊ ምላሽ እና እርምጃ በመውሰድ የወረርሽኙን ግስጋሴ በአጭር ጊዜ እና የተፈራውን ያህል ጉዳት ሳያደርስ በመግታት…

አዳዲስ ችግሮች በአዳዲስ እርምጃዎች መፈታት አለባቸው!

መቼም ይኼ ኮሮና የማይገባበት ጉዳይ የለም፤ ይኸው በዚህ ሳምንት ደግሞ የምርጫውን መራዘም አስከትሎ የተፈጠረውን ሕገ መንግሥታዊ ችግር እንዴት እንፍታው በሚል ፖለቲከኞቻችንን እያጨቃጨቀ ይገኛል። የእነሱ ጭቅጭቅ የተለመደ ቢሆንም አሁን ያነሱት ጉዳይ ግን ከዚህ በፊት ካጋጠማቸው ለየት ያለ ነው። በነሐሴ ሊካሔድ የነበረው…

የሚሰበሰበው ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ግልጽ ስርዓት ይበጅ

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለማችን ከተከሰተና ሥርጭቱን በአራቱም ማዕዘናት ካስፋፋ በኋላ ኢትዮጵያንም ዘግየት ብሎም ቢሆን ጎብኝቷታል። ወረርሽኙ በአገራችን የተፈራውን ያክል አስጊ ደረጃ ላይ ባይደርስም እስካሁን ከ11,669 በላይ ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 117ቱ ቫይረሱ እንደያዛቸው፣ ሦስቱ ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ 87ቱ የሕክምና እርዳታ ክትትል…

ወረርሽኙን ለመግታት መንግሥት ጥብቅ እርምጃ ለመውሰድ አያመንታ!

ከቻይና ቀጥሎ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ማእከል ሆና በቆየችው ጣልያን የመጀመሪያው በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው ከታወቀ አሁን ኹለት ወር እንኳን አልሞላም። የ38 ዓመቱ ሰው በሰሜናዊ ጣልያን ሎዲ በምትባል የሚላን ክፍል ከተገኘ በኋላ የመጀመሪያዎቹ የአገሪቱ የቫይረሱ ተያዦች በአካባቢው ነበር የበዙት። ወረርሽኙ እየተዛመተ…

በዘመነ ኮሮና የጤና ባለሙያዎችን ከጎናችሁ ነን ልንላቸው ይገባል!

የኖቭል ኮረናን ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ሁለገብ ትግልና እንቅስቃሴ፣ ፊት ለፊት ተጋላጭ በመሆን የውጊያው ፊታውራሪዎች ሐኪሞች፣ ነርሶች እና የጤና መኮንኖች በአጠቃላይ የጤና ባለሙያዎች መሆናቸው አይታበይም። የጤና ባለሙያዎች በሥልጠና ከሚያገኙት እውቀት፣ ክህሎትና ጥበብ ባሻገር ሙያው መሰጠትን የሚጠይቅ ክቡር የሰው ልጅ…

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመከላከል ጎን ለጎን ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይፈጠር መሥራት ይገባል!

መነሻውን በቻይናዋ ዉኀን ግዛት ያደረገው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አራት ወራት እየተጠጋ ባለው የጊዜ ቆይታው ዓለምን በማዳረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በማጥቃት በአጠቃላይ ከ55 ሺሕ በላይ ሰዎችን በመግደል የአስፈሪነት ግስጋሴውን ቀጥሏል። ትኩረት ባያገኝም ወረርሽኙ ከያዛቸው መካከል ከ220 ሺሕ በላይ ሰዎች ከበሽታው…

ሁሉም አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል!

የጤና ዘርፋቸው ያልጎለበተ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች በበለፀጉት አገሮች በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ኮቪድ-19 ቫይረስን ለመቋቋም ያላቸው ዝግጁነት እጅጉን አናሳ ነው። በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ከፍተኛ ክትትል በሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ ሊያገኟቸው የሚገቡት እንደ ቬንቲሌተር ዓይነት የሕክምና ማገዣዎች ቁጥር አናሳ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com