የእለት ዜና
መዝገብ

Category: ዓውደ-ሐሳብ

ቅጥ ያጣ የመንግሥት አባካኝነት ሙስና እና የዋጋ ግሽበት

ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ተብሎ በድፍረት ሊጠቀስ በሚችል ውስብስብና በርካታ ችግር ውስጥ ትገኛለች። ሰላም ማጣትን ተከትለው የሚመጡ ጦሶች ሁሉ ደርሰዉባታል፤ አሁንም እነዛኑ እየታገለች ትገኛለች። መምህር እውነቱ ይታይ ከአዲስ አበባ ባሰፈሩት አጠር ያለ ጦማር ደግሞ፣ በተለይ ለዋጋ ግሽበትና አሁን በኑሮ ላይ ለተፈጠረው…

ሚናዬ!

ግዜው ወደ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ይሆናል። ታክሲ ለመጠበቅ ረጅም ሰዓት ስለፈጀብን እየተማረረ ነው። ታከሲ ውስጥ ገብተንም፤ ቀናቱን ያማርራል። ተራ አስጠባቂዎችን ይተቻል። መንግስትነ ይራገማል። ህዝብና ሀገርን ይሳድባል፤ በወር ገቢ ማነስ ያጉረመርማል። ዐብሮት ያለው ጓደኛው ከጥቂት ፈገግታ ጋራ ግድ ባልሰጠው መንገድ…

በእንተ ትምህርት!

ሁሉንም እንዳወቀ የሚያስብ ተጨማሪ ለማወቅ ስለማይጥር የሚተላለፍለትንም ዕውቀት ስለማይቀበል እንደሞተ ይቆጠራል ይባላል። ትምህርት ማለቂያ የሌለው የሥልጣኔም ሆነ የፅድቅ መንገድ እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ ትውልድን ለማብቃት የሚደረገው ተግባር ግን ከሚጠበቀው በጣም የወረደ እንደሆነ ይነገራል። ከቀደሙት ኢትዮጵያውያን ምሁራን መካከል ስለትምህርት አስፈላጊነት ያመኑበትንና ያወቁትን…

ምዕራፍ አንድ ሳይገባን!

ምዕራፍ አንድ የሁሉ መሠረትና ትኩረት ያልተሰጠው ጉዳይ ነው የሚሉት በድሉ አበበ፣ በሁሉ ነገር መግቢያ የሆነውን የመጀመሪያ ክፍል የሚያስተውል ሰው ምን ያህል ትርፍ እንደሚያስገኝ ያብራራሉ። ልክ የሀይማኖት መጻሕፍትንና አስተምህሮን የመጀመሪያ ክፍል እንደማወቅና እንደመረዳት ነው። ይህም ፍቅር ነው። ምዕራፍ አንድ ሲገባን ፍቅርና…

የዐስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድና ፈታኙ የመጀመሪያ የትግበራ ዓመት

አገራት ሕዝባቸውን ወደ እድገት ጎዳና ለመውሰድ በየተወሰኑ ዓመታት የሚከለስና ተግባራዊ የሚደረግ ዕቅድን አውጥተው ያስፈጽማሉ፤ መከናወኑንም እየገመገሙ ተግባራዊ ያስደርጋሉ። ኢትዮጵያም ተመሳሳይ መንገድን እየተከተለች፣ የሕዝብን ፍላጎት የሚያሟላ የሚባሉ ዕቅዶችን የተለያዩ መንግሥታት ይፋ ሲያደርጉ ኖረዋል። በቅርቡም ‹የዐስር ዓመት ዕቅድ› የሚባል ተሠርቶ ዕቅዱን ተግባራዊ…

“ወንጀል የፈጸምኩት ተገድጄ ነው” ማለት ከተጠያቂነት ያድናል?

‹አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም› የሕግ መሪና ቀዳሚ ጽንሰ ሐሳብ ነው። ሕግ ዕያወቁ የሚያጠፉን ኹሉ የሚቀጣ ሲሆን፣ አልፎም ‹ስለማላውቅ ነው› ላለ ምህረት ሊሰጥ ይገባል የሚል አይደለም። በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በተነሳውና ዓመትና ወራትን በተሻገረው ጦርነት መካከል በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል። ይህ ትልቅ…

አልን ተባልን አስባልን ይባላል

ዓለም በብዙ ለውጦች ውስጥ አልፋለች። በድሉ አበበ በአፍሪካ እንዲሁም በተለያዩ አገራት የተፈጠሩ ለውጦችንና ለለውጦቹም መነሻ የነበሩ ማዕበል ያሏቸውን አመጽና ትግሎች በምልሰት አንስተዋል። ‹መነሻ ሐሳቡ የወሰድኩት ከደራሲ አብረሃም ረታ ዓለሙ (ነፍሰ ኄር) “አልን፤ ተባልን፤ አስባልን ይባላልና ሌሎችም” መጽሐፍ ነው ብለው፤ ወደኋ…

ኢንዱስትሪዎቻችን ለገጠማቸው የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር ዘላቂው መፍትሄ ምንድነው?

የግብርና ዘርፍ ልማት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ አገራት በበርካታ ተቋማዊ ችግሮች የተተበተበ ነው። ይልቁንም ወጥነት ያለው የጥሬ ዕቃና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ሰለባ በመሆኑ በተፈለገው ልክ እንዳያድግ ሆኗል። ሽመልስ አረአያ (ፒኤችዲ) ይህን ነጥብ በማንሳት በተለይም አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች የገጠማቸውን የጥሬ ዕቃ…

መንትዮቹን አትለያዩዋቸው

በኢትዮጵያ በሕዝቦችና በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የተነሱ ግጭቶች በታሪክ ተመዝግበው ይገኛሉ። እነዚህ ግጭቶች የግጦሽ መሬትን ጨምሮ ዛሬ ላይ ቀላል በሚመስሉ እንዲሁም ደግሞ በሌሎች መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ምክንያት የተነሱ ናቸው። አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶች፣ ጦርነት፣ አሰቃቂ ግድያና የእርስ በርስ መጫራረሶች ግን…

በሲዖል ውስጥ ወደ ገነት ጉዞ

ለወደፊት ትልቅን መመኘትና ማለም ጥፋት አይደለም። የሚቀድመውና ለነገም መሠረት የሚሆነው ግን ዛሬ ነው። የነገ ሕልምም ሆነ ግብ ስኬታማ እንዲሆን እንቅስቃሴ መጀመር ያለበት ዛሬ ነው። ተስፋን አሻግሮ ማየት ባያስኮንንም፣ አሁን እንደ ሲኦል አስፈሪና የከበደ ችግር ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ፣ ‹ወደ ውጪ አገር…

ዋ! ውኃ

ድርቅ በየተወሰነ ዓመቱ እየተከሰተ አገራችንን ለከፋ ጉዳት እየዳረገ የሚገኝ የተፈጥሮ አደጋ ነው፡፡ ይህን የተፈጥሮ ክስተት የሚያባብስ የሠው ልጅ ተግባር የመኖሩን ያህል፣ ጉዳቱን ለመቀነስ የሚደረግ ተግባር ደግሞ አናሳ መሆኑ ይነገራል፡፡ መፍትሔ የሚባሉ ዕርምጃዎችን ለማከናወን በመጀመሪያ የውኃ ዑደቱን ማወቅ ግድ ይላል፡፡ ከተፈጥሮ…

ስለሦስቱ ክብሮች

መከባበር ለሠው ልጆች እጅግ አስፈላጊ ከሚባሉ አብሮ ለመኖር ከሚያስፈልጉ ባህሪያት መካከል ከዋናዎቹ ተርታ ይመደባል። ክብር ለብዙ ነገሮች እንደሚሠጥ ኹሉ፣ ለሠው ብቻ ሳይሆን ለፍጥረታትም ሆነ የሠው ልጅ ለሠራቸውና ለመሠረታቸው ሥርዓቶችና ሒደቶች መሠጠት እንዳለበትም ይታመናል። በዚህ ክፉ እየተባለ በሚገለጸው ዘመን፣ ታዋቂዎች በሚዘለፉበት፣…

የቤት ባለዕድል ወይስ ባለዕዳ? ተበዳይ ነኝ -ከቦሌ በሻሌ

የዛሬ ሦስት ዓመት የካቲት 27 ቀን 2011 ኹሉም የአዲስ አበባ ነዋሪ ዐይኑን ቴሌቪዥን መስኮት ላይ አፍጦ የ13ኛ ዙር 20/80 እና የኹለተኛ ዙር 40/60 የቤት ዕጣ አወጣጥ ይከታተል እንደነበር የሚታወስ ነው። በወቅቱ ወደ 18 ሺሕ የሚሆኑ የ40/60 እና ወደ 32 ሽሕ…

ስድስት ባርኔጣዎች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስብሰባዎች የሠራተኛውን ጊዜ የበለጠ እየወሠዱ ይገኛል፡፡ አጨቃጫቂ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም ስለሌላቸው ብዙ ጊዜን እንደሚወስዱ፣ ሀብትንም እንደሚያባክኑ ይነገራል፡፡ “በሌላ ሠው ጫማ ውስጥ ሆነን ዕንመልከት” እንደሚባለው የውይይቶችንም ሆኑ የኮሚቴ አሠራሮችን ለማሻሻል ይጠቅማል ያሉትን ሐሳብ ታደሰ ብሩ ኬርስሞ (ዶ/ር)…

የመጠበቅ ኃላፊነት የአገሮችን ሉዓላዊነት መጣሻ ሰበብ

የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት በተለይ በአፍሪካ አገራት ራሱን የቻለ ጉዳይ ሆኖ መነሳት የሚችል ሰፊ አርዕስተ ነገር ነው። ታድያ ብዙ ጊዜ ለዚህ ጣልቃ ገብነታቸው ‹የመጠበቅ ኃላፊነት› የሚል ምክንያት ይጠቀሳል። ሽመላሽ ወንዳለ ይህን ነጥብ መነሻ በማድረግ በዚህ ጽሑፋቸው ስለ ‹የመጠበቅ ኃላፊነት› እና ተግባራዊነት…

የተሟላ ዕውቅና ያላገኙ መንግሥታት

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በርካታ አገሮች በጊዜ ሒደት ሲሠፉ አሊያም ሲፈርሱ ኖረዋል። እንደየአገራቱ ታሪክ ሒደቱ ቢለያይም፣ አገር ሲፈርስ ትናንሽ ግዛቶች ራሳቸውን ችለው እንደአገር ለመቆየት የማያባራ ጦርነት ውስጥ ሲገቡ ቆይተዋል። ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ እንኳን ጥቂት የማይባሉ አገራት የትላልቅ አገራትን መፍረስ ተከትሎ…

አገራዊ መግባባት ይበል የሚያሠኝ ዕርምጃ ነዉ

በኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ አገራዊ ልዩነቶች ሲመጡ በውይይት ከመፍታት ይልቅ፣ በጉልበት ለመፍታት የሚወሰድ ዕርምጃ እንደሚበልጥ የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ። በተለይ ባለፉት ሦስት መንግሥታት በሕዝብ ዘንድ የነበሩ ጥያቄዎችና የሚነሱ ልዩነቶችን በንግግር መፍታት ስላልተቻለ ጉዳዮቹም ሆኑ ችግሮቹ እስካሁን ዕልባት ሳያገኙ መቆየታቸው ይነገራል። እነዚህን ልዩነቶች…

የሠራዊቱ ወደ ትግራይ አለመግባት

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጦርነት ከተጀመረ አንድ ዓመት ከኹለት ወራት ገደማ ሁኗል። በዚህ ጊዜ ውስጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን አካል ሕግ ፊት ለማቅረብና ከአስጊነት ደረጃ ለማውረድ በርካታ ሰዎች መሰዋዕት የሁኑባቸው ውጊያዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። መከላከያ ትግራይ ክልልን ትቶ ከወጣ…

አውቆ የተኛው ዲፕሎማሲ

ዲፕሎማሲ ለአንድ አገር ኅልውና ልክ የመከላከያ ኃይልን ያህል አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ በኃይል ብቁ ሆኖ መገኘት የመጠበቁን ያህል በሥነ-ልቦናና በመረጃም ኹሌ ዝግጁ ሆኖ መገኘት ከየትኛውም መንግሥት ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲፕሎማሲ ረገድ የሚፈለገውን ያህል እንቅስቃሴ ባለማድረጓ አሁን ለገባንበት ችግር እንደአንዱ…

የሰላይና ሥራ አጥ ነጮች ክምችት ትኩረት ይሻል

ምዕራባውያን ኢትዮጵያን የመሳሰሉ በማደግ ላይ ያሉ አገራትንም ሆነ ተቀናቃኝ የሆኗቸውን የምሥራቅ አገሮች ሠላዮችን በመላክ አዳክሞ ለመበዝበዝና በዘመናዊ ቅኝግዛት ሥር ለማማቀቅ እንደሚሠሩ ይነገራል። በግብረ-ሠናይና በዓለም አቀፍ ተቋማት ሽፋን እየገቡ ከሙያው ጋር የማይገናኙ ብቃት የሌላቸውን የአገራቸውን ሥራ አጦች፣ እንዲሁም ጥቂት ብቁ የየአገራቱን…

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሚይዙት ጦር መሣሪያ ከኪስማዮ እየተጓጓዘ ይሆን?

የምሥራቅ አፍሪካ ወቅታዊ ሁኔታ ለብዙ ሕገ-ወጥ ተግባራት በር እየከፈተ እንደሚገኝ ይነገራል። በሶማሊያ ለዘመናት የዘለቀው የእርስ በርስ ግጭት ለአሸባሪዎችም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረ ይሰማል። ይህን ለመግታት የኢትዮጵያና ኬንያ መንግሥታት የየራሳቸውን መፍትሔ ሲሞክሩ ቆይተዋል። ለቀጠናው አለመረጋጋት ጎሳዊ አስተሳሰብ በር መክፈቱ ቢነገርም፣ ሁኔታውን ያባባሰ…

አሜሪካ ለምን በአፍሪካ ቀንድ ያልተገባ ጫና መፍጠር መረጠች?

የዋሽንግተን ሰዎች ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጡት ብሔራዊ ጥቅም (National Interest)ን ነው ። ያ ደግሞ የደኅንነት እና ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎታቸውን ስጋት ላይ የሚጥል መስሎ ከታያቸው ብቻ ነው ። ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ ላይ እንዴት? የሦስቱ የአሜሪካ ሥጋቶች፡- 1) የኢትዮጵያ፣ኤርትራ እና ሱማሊያ ጥምረት…

ምርጫ ቦርድ መብታቸውን የነጠቃቸው ሕዝቦች!

መስከረም 24 በተካሔደው በዓለ ሲመት ላይ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ፣ በርካቶች በፍላጎትም ይሁን በተልዕኮ መገኘታቸው ይታወቃል። ዕለቱ የአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ እንግልትና ከፍተኛ ወጪ ያስከተለ ነበር የሚሉት ግዛቸው አበበ፣ በዕለቱ የብልጽግና መሪ የሆኑት ዶ/ር ዐቢይ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የታጩበትና የተመረጡበት መንገድ የብዙዎችን…

የእርስ በርስ ጦርነት ማስወገጃ መፍትሄ

ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች የመከሰቱን ያህል መፍትሄውን ለማወቅ መንስዔውን ማወቁ አስፈላጊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ የመጣው የርስበርስ ግጭት መንስዔ በዋናነት ያልተመጣጠነ እና ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል ነው የሚሉት ሳምሶን ኃይሉ፣ መፍትሔ ነው ስላሉት ገለልተኛና አካታች ተቋማትን መገንባት ላይ…

የነጻነት ትግል፤ የደካሞች ዕርግማን?

የነጻነት ትግል እየተባለ ሕዝቦች እርስበርስ መጠፋፋት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ያልተሳካላቸው የመኖራቸውን ያህል ሕዝብን ለያይተው ለጉስቁልና እንዲሁም ለኃያላን መፈንጫ ያደረጉ የየዘመኑ ልኂቃን መኖራቸውን አዲሱ ደረሰ በጽሑፋቸው ያትታሉ፡፡ የፓናማ እንደአገር መመስረትን ታሪክ እያጣቀሱ የሱዳን ልኂቃንም ሆኑ የትግራዮቹ ራሳቸውን አኮስሰው ጉልበተኛ የውጭ አገራን ከሚያገዝፉበት…

የእርስ በርስ ጦርነት ዐቢይ መንሥዔ

‹እግርና እግርም ይጋጫል› የሚለው ኢትዮጵያዊ ብሂል በአንድ ሥም የሚጠሩ፣ የሚጋሯቸው ብዙ እሴት ያላቸው ሰዎች መካከል ሳይቀር ግጭቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ያስረዳል። በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ግጭቶች ዋና መንስዔ የዘውግ ፖለቲካ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ሰበብ ማለትም ፍትሃዊ ያልሆነ የሀብት ክፍፍል ያስከተለው ችግር ነው ይላሉ፤…

የአሜሪካው የመስከረም 11 ጉድ!

መስከረም 1 ቀንን አይረሴ ከሚያደርጉ የቅርብ ታሪኮች መካከል በአሜሪካዎቹ የኒውዮርክ መንትዮቹ ህንፃዎች ላይ ተፈፀመ የተባለው የሽብር ጥቃት በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል፡፡ በዓለማችን ላይ የታሪክ አቅጣጫን የቀየረው ይህ ክስተት በብዙ አሉባልታዎችና ምስጢሮች የታጀበ ነው፡፡ ጥቃቱን ማን ፈፀመው? የአሜሪካ መንግስትስ እጁ አለበት ወይ?…

የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በኢትዮጵያ

በሴቶች ላይ የሚፈጸም አድሎ እየቀነሰ መጥቷል ቢባልም የጾታ እኩልነትን ከማስገኘት አኳያ ብዙ ሥራ እንደሚቀር በርካቶች ይናገራሉ። አድሏዊነቱ ስር እንደሰደደ ከሚያምኑትና የኹላችንንም ሥራ ይጠይቃል ከሚሉ ሴቶች መካከል ፍቅር ሽፈራው አንዷ ናቸው። ላለፉት 6 አመታት ሴቶችን ለማብቃት በስርዓተ-ጾታ ዘርፍ ለሚሠሩ አካላት የማማከር…

የመሪ ያለህ!

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ወታደራዊ ዘመቻ ከተጀመረ አንስቶ በርካታ ስህተቶች እንደተፈፀሙ የሚናገሩ አሉ። ከእነዚህ መካከል መከላከያ ትግራይን ለቆ የወጣበትን ምክንያት የማይቀበሉ ድርጊቱን ሲተቹት ይሰማል። ይህን ተግባር ደርግ ትግራይን ለቆ ከወጣበት ሂደት ጋር እያነፃፀሩ ግዛቸው አበበ እንዲህ ያስነብቡናል። ቤኒሻንጉል ክልል አንዴ ወያኔዎች፣…

የድምበር ተሻጋሪ ወንዞች ዓለማቀፍ የውኃ ፖለቲካና የኢትዮጵያ ሁኔታ

የዓባይ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ በዓባይ የመጠቀም መብት ያላት ከመሆኑ በላይ የማንንም ጥቅም የማትነካ መሆኑ በተደጋጋሚ ቢገለጽም፣ አገራት ኢትዮጵያ ይህን እንዳታደርግ ውጥረት ውስጥ ከመክተት አልታቀቡም። የድምበር ተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም የተመለከተ ጉዳይ ሲነሳ አገራት ይህን ጉዳይ የሚያስተናግዱበት አካሄድ አላቸው። ለዚህ ሕግ ምንጭ…

error: Content is protected !!