መዝገብ

Category: አቦል ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም በቪፒኤን አገልግሎት ላይ የ 72 በመቶ ቅናሽ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ለወራት ሲያካሂድ የቆየውን የማስፋፊያ ስራ በማጠናቀቅ በቪፒኤን አገልግሎት ላይ የ 72 በመቶ ቅናሽን ጨምሮ የፍጥነት እና የዋጋ ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታወቀ። ቴሌኮሙ ዛሬ በሽራተን አዲስ እያካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ይፋ እንዳደረገው ከ 12 ሚሊዮን ዶላር ባላይ ወጪ ያደረገበትን ይህንን…

መንግሥት ማዳበርያ አስኪያስገባ አስመጪዎች የወደብ እንዲከፍሉ ተገደዱ

ማዳበሪያውን ማስገባት ለሚቀጥሉት ኹለት ወራት ይቀጥላል የኢትዮጵያ መንግሥት 1.5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ እያስገባ መሆኑን ተከትሎ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ የነበሩ ኮንቴይነሮች የወደብ ኪራይ እየከፈሉ በጅቡቲ ወደብ እንዲቆዩ ተደርገዋል። ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በአስመጪ እና ላኪነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 7.5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ብድር ከንግድ ባንክ ወሰደ

ተቋሙ በገንዘብ እጥረት የተነሳ ፕሮጀክቶች ለማቆም ጫፍ ደርሶ ነበር ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ወድቆ የነበረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያለበትን የብድር ወለድ ለመክፈል እንዲሁም ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ለሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ማስገንቢያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰባት ነጥብ…

ሕገወጥ ምንዛሬን ሕጋዊ ለማድረግ አይ ኤም ኤፍ እና ብሔራዊ ባንክ ጥናት ሊያደርጉ ነው

በሕገ ወጥ መንገድ በውጭ ምንዛሬ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መንዛሪዎችን ሕጋዊ በሆነ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ፣ ከፊታችን ሰኞ የካቲት 16/2012 ጀምሮ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ እና ብሔራዊ ባንክ ጥናት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለፀ። ብሔራዊ ባንኩ በቀጣይ ሦስት ዓመታት…

በጋምቤላ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ የሌላቸው ኮሌጆች ትምህርት እየሰጡ ነው

በጋምቤላ ክልል 11 ኮሌጆች የከፍተኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ፍቃድ ሳይኖራቸው ተማሪዎችን በመመዝገብ የከፍተኛ ትምህርት እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ። ኮሌጆቹ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ምዘና ኤጀንሲ ከፍተኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ሳይሰጣቸው፣ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ደረጃዎች…

በወላይታ ዞን ብሔርን መሠረት ባደረገ ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በወላይታ ዞን አረካ ወረዳ ብሔርን መሰረት አድረጎ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ንብረት መውደሙን በአካባቢው የሚገኙ ግለሰቦች ለአዲስ ማለዳ ገለፁ። ጥቃቱ ጥር 22/2012 የተፈፀመ ሲሆን፣ በወላይታ ዞን አረካ ወረዳ ውስጥ ስልጤ ሰፈር በተባለ እና ከስልጤ አካባቢ ለሥራ ወደ ቦታው ሄደው ኑሯቸውን እዛ…

የጥጥ ዋጋ ባለፉት ሳምንታት ከኹለት እጥፍ በላይ ጨመረ

የጥጥ ዋጋ በ20 ቀናት ውስጥ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ ማሳየቱን ባህላዊ ልብሶችን የሚያመርቱ ማኅበራት ገለፁ። አንድ ኪሎ ጥጥ ከ20 ቀናት በፊት ከ50 እስከ 70 ብር በሆነ ዋጋ ሲገዙ እንደቆዩ የገለጹት ማኅበራቱ፣ አሁን ግን ይኼው መጠን ጥጥ እስከ 230 ብር እየተሸጠ…

አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በ2 ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባ ዋና መሥሪያ ቤት እየገነባ ነዉ

ከአንድ ዓመት በኋላ ዋና መሥሪያ ቤቱን ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋር አቅዷል የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የፋይናንስ ዲስትሪክት ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ዋና መሥሪያ ቤቱን ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር በኹለት ቢሊዮን ብር ሕንፃ እያስገነባ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ17 ሺሕ ሠራተኞቹ የብድር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ከአፍሪካ በትርፋማነቱ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ17 ሺሕ በላይ ሠራተኞቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የብድር አገልግሎች መጀመሩን አዲስ ማለዳ አረጋገጠች። ባንኮች ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት በገጠማቸው ወቅት ተግባራዊ የተደረገው አገልግሎቱ፣ ከታችኛው የሥራ መደብ እስከ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። አየር መንገዱ…

15 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በምሥረታ ላይ ናቸው

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ተቆጣጣሪ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 15 የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በምሥረታ ላይ መሆናቸውን ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የተለያዩ ማሻሻያዎች ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ፣ በርካታ የፋይናንስ ተቋማት በምሥረታ ላይ ሲሆኑ፣ አዳዲሶቹ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት…

‹‹የፓርቲ አባል በመሆናቸው የታሰሩ ዜጎች የሉም›› የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የፓርቲ አባል በመሆኑ በጸጥታ ኃይሎች የታሰረ ዜጋ የለም ሲል ከዚህ ቀደም የቀረበበት ወቀሳ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታወቀ። ባለፉት ኹለት ሳምንታት ወስጥ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላቶቻችን ታስረውብናል ቢሉም፣ የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ የፓርቲ…

ሂጅራ ባንክ በ700 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ሥራ ለመጀመር የብሔራዊ ባንክን ፈቃድ እየጠበቀ ነው

በምሥረታ ላይ ከሚገኙት የእስላሚክ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ሂጅራ ባንክ የአክሲዎን ሽያጭ መጨረሱን ተከትሎ፣ በ700 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ወደ ሥራ ለመግባት የብሔራዊ ባንክን የፍቃድ ማረጋገጫ እየጠበቀ መሆኑ ታወቀ። የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር መከሚል በትሩ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ሂጂራ ባንክ ቅድመ…

የኤክሳይስ ታክሱን አዋጅ መጽደቅ ተከትሎ ዋጋ መጨመሩ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ

‹‹ ሕጉ ተፈፃሚ እንዲሆን አያስገድድም›› የኤክሳይስ ታክሱ አዋጅ የካቲት 5/2012 በተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን ተከትሎ ታክሱ በተጣለባቸው እንደ ቢራ ያሉ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ የሕግ አተገባበር ጊዜውን የጠበቀ አይደለም ተባለ። የታክስ ጉዳዮች እና የሕግ ባለሙያ የሆኑት ዮሐንስ ወልደገብርኤል…

ጁነዲን ሳዶ ሸገር የተሰኘ አዲስ ባንክ ሊመሠርቱ ነው

የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ ‹ሸገር› የተሰኘ አዲስ ባንክ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። የባንኩ መሥራች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ጁነዲን ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ድርሻ የመሸጥ ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝተው ከየካቲት ሰባት ጀምሮ በይፋ አክስዮን መሸጥ…

ኤጄቶ የሲዳማ ክልል ርክክብ እስከ የካቲት 15 እንዲካሄድ ጠየቀ

እስከ የካቲት 15 ድረስ የሥልጣን ርክክብ ተካሂዶ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ የማይከናወን ከሆነ የሲዳማ የወጣቶች ቡድን የሆነው ኤጄቶ ተቃውሞ እንደሚያስነሳ አስጠነቀቀ። ሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን የቻለ ክልል መሆኑን በድምጹ ካረጋገጠ ሦስት ወራት ቢቆጠሩም ገዢው ፓርቲ የሲዳማን ክልል…

የድንጋይ ከሰል ከውጪ ማስገባት ሊቆም ነው

በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት ለመጠቀም እና ከወጪ አገራት የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ለመተካት በመታሰቡ የድንጋይ ከሰል ከውጪ አገራት እንዳይገባ ሊደረግ ነው። ከውጪ አገራት የሚመጣውን የድንጋይ ከሰል ምርት ማስቆም ያስፈለገው፣ ኢንዱስትሪዎች በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት መጠቀም…

ሲጋራ በፓኬት የ15 ብር ጭማሪ አሳየ

በኢትዮጵያ የሚመረቱ የሲጋራ ምርቶች ላይ ኻያ ፍሬ የሚይዝ አንድ ፓኬት ሲጋራ ከዚህ ቀደም ሲሸጥበት ከነበረው 25 ብር ዋጋ ወደ 40 ብር፣ የ15 ብር ጭማሪ አሳየ። ምንም እንኳን የምርት ዋጋ ላይ ጭማሪ ባይኖርም፣ አከፋፋዮች በኤክሳይስ ታክስ ምክንያት በሚኖረው የዋጋ ጭማሪ ላይ…

ብልፅግና ፓርቲ በ40 ሚሊዮን ብር አዲስ ጽሕፈት ቤት ሊገነባ ነው

ብልፅግና ፓርቲ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለሦስት ወለል የጽሕፈት ቤት ሕንፃ ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ። ግንባታው በያዝነው ዓመት ተጀምሮ በቀጣይ ኹለት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል የተባለ ሲሆን፣ የፓርቲው የዞን ኃላፊዎች እና ድጋፍ ሰጪ…

ኢትዮጰያ ለኤርትራዊያን ስትሰጥ የቆየችውን የቡድን ጥገኝነት አቆመች

የኢትዮጵያ መንግሰት ላለፉት ሶስት አመታት ከኤርትራ ድንበር አቋርጠው ለሚመጡ ኤርትራዊያን የቡድን እውቅናን መሰረት በማድረግ ጥገኝነት በመስጠት ስታስተናድ ብትቆይም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ግን ይህንን ማቆሟን አስታወቀች፡፡ ይህም ከተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ወቀሳ እያስነሳ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት የስተደተኞችን ስምምነት የጣሰ ነው ተብሏል፡፡…

አንበሳ ጋራዥ በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደ ዴፖ ሊቀየር ነው

ከሃምሳ ዓመት በላይ የአንበሳ አውቶቡስ ማቆሚያ እና የጥገና ቦታ ሆኖ ያገለገለው ዋናው መሥሪያ ቤት፣ በአንድ ጊዜ ከ850 በላይ አውቶቡሶችን ማስተናገድ እንችልና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ‹‹የካ ዴፖ›› በሚል ግንባታ ሊከናወንለት ነው። በሦሰት ወራት ውስጥ የሚጀመረው ይህ ግንባታ፣ ኹለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን…

በደቡብ ኦሞ የኮሌራን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የኬሚካል እጥረት አጋጥሟል

በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ወረዳዎች ከታኅሳስ 15/2012 ጀምሮ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ውሃን ለማከም የሚያገለግሉ ኬሚካሎችን ለማግኘት እና የትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ችግር እንደገጠመው ዞኑ አስታወቀ። ወረርሽኙ በዞኑ ማሌ፣ ሀመር፣ ሰላማቦ እና ፀማይ በተሰኙ ወረዳዎች ላይ ከተከሰተ ከአንድ ወር 15 ቀን…

የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሥልጠና በመንግሥት ወጪ መደረጉ ቅሬታ አስነሳ

የመንግሥት ተንቀሳቃሽ ሂሳቦች ዝግ ሆነው ቆይተዋል ብልፅግና ፓርቲ ከመስተዳድር ጀምሮ እስከ ዞን ላሉ የቢሮ ኃላፊዎች እና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ እየሰጠ ላለው ሥልጠና የውሎ አበልን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን ከመንግሥት ካዝና እንዲሸፈን መደረጉ ቅሬታ አስነሳ። ለፓርቲው አባላት እና ከክልላዊ መስተዳደር…

የሜቴክ ሰራተኞች አራት መኪኖች አቃጠሉ

የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቢሾፍቱ ባስ መገጣጠሚያ ሠራተኞች የተገባልን የደሞዝ ጭማሪ ይፈፀምልን በሚል ምክንያት ከሦስት ሳምንት በፊት አራት አውቶቡሶችን አቃጠሉ። ከ 10 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ በተደጋጋሚ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ለሠራተኞቹ ቃል ቢገባም መፈፀም አልቻለም። በዚህ ምክንያት…

ብሔራዊ ባንክ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

ጭማሪው የሰራተኞችን የስራ ደረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ የተደረገ ነው ብሔራዊ ባንክ ከጥር 01/2012 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ለሠራተኞቹ አደረገ። ባንኩ ከ50 በመቶ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ ማድረጉን ለሠራተኞቹ በላከው የውስጥ ደብዳቤ ላይ…

በኢትዮጵያ የሚነሱ ግጭቶችን በየሦስት ወሩ መተንተን ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ተቋም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በየሦሰት ወሩ የሚመዘግብ፣ የሚተነትን እና ይፋዊ ሪፖርት የሚያወጣ አዲስ ቡድን አደራጅቶ ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ። የመንግሥት ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የተለያዩ የግል ድርጅቶች እንዲሁም የሚዲያ ተወካዮች በዚህ ሥራ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘዴዎች…

በዋግ ኽምራ ዞን 108 ሺሕ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋለጡ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በ2010 የክረምት ወቅት የዝናብ እጥረት በማጋጠሙ በተለይም በዝቋላ፣ በሳሃላ እና በሰቆጣ ወረዳዎች ባጋጠመው ድርቅ ለቀጣይ አምስት ወራት 108 ሺሕ ዜጎች አስቸኳይ የእለት የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ። ችግሩ በከፋባቸው ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ውሃ ወዳለባቸው…

የታኅሳስ ወር የቡና ወጪ ንግድ ቅናሽ ተመዝግቦበታል

በታኅሳስ ወር ወደ ውጪ አገራት የተላከው የቡና መጠን ቢጨምርም የተሰበሰበው ገንዘብ መጠን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ4 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱ ተገለፀ። ባሳለፍነው ወር ቡናን ወደ ውጪ አገራት በመላክ 14 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን፣ የወሩ የቡና…

አንድ የመሥሪያ ቦታ ለኹለት ኢንተርፕራይዞች መሰጠቱ እያወዛገበ ነው

በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የአፈር መድፊያ ቦታ በማስተዳደር ሥራ ላይ የተሰማሩ ኹለት ኢንተርፕራይዞች ተመሳሳይ ቦታ ላይ ሕጋዊ ፈቃድ ይዘው መገኘታቸው ግርታ ፈጥሯል። የእነ መስፍን ኢንተርፕራይዝ እና የተከሰተ ዮሐንስ እና ጓደኞቹ ኢንተርፕራይዝ የተባሉ በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች፣ በቡልቡላ አካባቢ…

የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ለአምስት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያውን ድጋፍ አደረገ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ በቀን አንድ ዶላር ከዲያስፖራው ህብረተሰብ በጠየቁት መሰት የተሰበሰበ ገንዘብን የልማት ስራዎች ለማዋል በቀረበ ጥሪ መሰረት ተወዳድረው ላሸነፉ አምስት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያውን ገንዘብ ለቀቀ። ከዚህ ቀደም ትረስት ፈንዱን ከሚስተዳድረው ቦርድ በወጣ ማስታወቂያ መሠረት 466 ፕሮጀክቶች ንደፈ ሀሳብ ያቀረቡ…

የስድስት ወር የጨርቃጨርቅ የወጪ ንግድ የ 900 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አሳየ

በ2012 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ወደ ውጪ ከተላከው የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ903 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳየ። በዘርፉ ከተሰማሩ የውጪ እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች በአጠቃላይ 99.86 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ከእቅዱ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com