መዝገብ

Category: የእለት ዜና

ሰሞኑን በጋሞ ዞን እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ናዳ በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በናዳው ምክንያት ከቆጎታ ወረዳ ኦቴ ቀበሌ 3ሰው ሲሞት አንድ ሰው ላይ ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል። በዘኑ የሚገኙ 21 አባወራ 176 የቤተሰብ አባላትም መፈናቀላቸውን የጋሞ ዞን አደጋ ስጋት ስራ-አመራር ጽኀፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ማርቆስ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዞኑ ቁጫ ወረዳ ሾጮራ…

በእነ እስክንድር ነጋ ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጠ

ፍርድ ቤቱ  እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ግለሰቦች ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ትእዛዝ ሰጥቷል።   የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት አቃቤ ህግ ከዚህ በፊት የመሰረተው ክስ አጠቃላይ ዋስትና ላይ ዝርዝር…

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 12/2013 እያካሄደው ባለው በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅለይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  (ዶ/ር)  የቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡ ቀነዓ ያዴታ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር 2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ…

በእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ጥያቄ እና የዐቃቤ ሕግ ተቃውሞ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት እነ  እስክንድር ነጋ በጠየቁት የዋስትና መብት እና የዐቃቤ ሕግ ምላሽ ላይ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመስከረም 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ያዘ። እስክንድርን ጨምሮ ሰባት ሰዎች የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ እና…

በአፍሪካ  50 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በከፋ የድህነት ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ ተባለ

አፍሪካ በአሁን ወቅት የዓለም ስጋት በሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በዘንደውሮው በፈረንጆቹ በ2020 መጨረሻ ላይ 13 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ ከድህነት ወለል በታች  ይወድቃሉ ተብሎ  ሲጠበቅ ወደ 50 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ  በከፋ የድህነት ደረጃ ላይ ሊደርሱባት ይችላል ተብሎ እንደሚገመት የቢል እና…

በአምስት ክልሎች ላይ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 217 ሺህ ሠዎች ተፈናቀሉ

በኢትዮጵያ ባለፉት የክረምት ወራት በአምስት ክልሎች፣በ 40 ወረዳዎች እና በ25 ዞኖች ላይ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 580 ሺህ ሠዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን  217ሺህ የሚሆኑት  ደግሞ መፈናቀላቸውን የሠላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ። ባለፉት ሦስት ወራት በአንዳንድ አካባቢዎች የዘነበው የዝናብ መጠን ከፍተኛ…

ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምትቀይራቸው የብር ኖቶች 3ነጥብ6 ቢሊዮን ብር ወጪ አወጣች

ኢትዮጵያ ለ23 ዓመታት ያህል  ስትጠቀምባቸው የነረበሩትን  የብር ኖቶችን መቀየሯ ይፋ ተደረገ። በዚህም 262 ቢሊየን መጠን ያላቸው የብር ኖቶች የታተሙ ሲሆን ለህትመቱም 3ነጥብ6 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ለኢትይዮጵያን  ቢዝነስ ሪቪው መጽሔት (EBR) ገልጸዋል። ነባሮቹን የ10፣…

በደጀኔ ጣፋ፣ መስተዋርድ ተማምና በጃዋር መሀመድ የኮምፒውተር ባለሙያ ላይ ክስ ተመሰረተ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ ኦፌኮ አመራር   ደጀኔ ጣፋ፣  መስተዋርድ ተማም እና በጃዋር መሀመድ የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ባለሙያ ሚሻ አደም ላይ ክስ መሰረተ። ክሱ በሁለት የተከፈለ ሲሆን አንደኛ ተከሳሽ ደጀኔ ጣፋ እና መስተዋርድ ተማም ላይ ሲሆን  ሁለተኛው በሚሻ አደም ላይ ነው።…

የቀድሞ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በህገ ወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም አሉ

  ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ቦታ ላይ ባልገኝም ከዚህ የመጓተት ፖለቲካ አስተሳሰብ መውጣት አለመቻል ግን ትልቅ ህመም እንደሆነ ይሰማኛ ያሉት የቀድሞው የአደስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር)  የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ…

ፍርድ ቤቱ በልደቱ ላይ ክስ እስከሚመሰርት መርማሪ ፖሊስ እንዲሰጠው የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ውድቅ አደረገ

ልደቱ አያሌው ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ አቃቤ ህግ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፖሊስ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም ሲል ውድቅ አደረገ።   ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ…

የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲውን በተመለከተ ቅሬታውን አሰማ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባጋጠመው ክስተት አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ የእንግሊዝ ኤምባሲ ከፍተኛ ባለስልጣን በይፋ ቅሬታቸውን አሰሙ። ቅሬታቸውን ያሰሙት በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅ ላይ ከሰሞኑ ለተቃውሞ በተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያን…

ፍርድ ቤቱ በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን መስማት ጀመረ

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ተረኛ ምድብ ችሎት በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን መስማት ጀመረ።   ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ እና የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቧቸው አቤቱታዎች ላይ ትእዛዝ ሰጥቷል። ጃዋር እና በቀለ ገርባ ያለ ፈቃዳችን ፎቶግራፍ እና…

የተከዜ የብረት ድልድይ በጎርፍ ተወሰደ

  የተከዜ የብረት ድልድይ በጎርፍ በመወሰዱ ምክንያት የነዋሪዎች እንቅስቃሴ መገደቡን የስሃላ ሰየምት ወረዳ አስታወቀ። ችግሩ በየዓመቱ ለሦስት እና ለአራት ወራት የሚዘልቅ መሆኑን የጠቀሰው ወረዳው፤ ከፊሉ የብረት ድልድይ በጎርፍ በመወሰዱ ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባም ጠይቋል። የስሀላ ሰየምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች…

ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች በመንግስት ኃላፊዎች ወደ ቤታችሁ ካልተመለሳችሁ እርዳታ አታገኙም የሚል አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ ተገቢ አለመሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተከሰተው የሰላም መደፍረስ ምክንያት የተከሰተውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሁኔታ ላይ  ምርመራ ማድረግ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን ኮሚሽኑ ባለፉት ሁለት ሳምንታትም ከ40 በላይ ችግሩ ተከስቶባቸዋል በተባሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ የምርመራ ቡድኖችን…

ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አንድ መንደር በሙሉ ኳራንቲን ተደረገ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ 24 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ከሌሎች አካባቢዎች በላቀ ሁኔታ በስፋት በመታየቱ አንድ መንደር በሙሉ ተለይቶ ኳራንቲን መደረጉ ታወቀ። የአዲስ ማለዳ ምንጮች ከስፍራው እንዳስታወቁት ስፍራው ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ውሃ ልማት…

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ ቻይና ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ ቻይና ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዋንግ ዪ በኩል አረጋግጣለች። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ከቻይና ስቴት ካውንስልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑት ዋንግ…

የኢራን መንግስት ዶናልድ ትራምፕን በቁጥጥር ስር ለማዋል የእስር ማዘዣ አወጣ

የኢራን መንግስት በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አልጀዚራ ሰበር ዜና ሲል ይዞ ወጥቷል። የእስር ማዘዣው በፕሬዝዳንቱ ላይ እንዲወጣም ምክንያቱ ከወራት በፊት የኢራኑ ጄኔራል ቃሴም ሶሌማኒ ኢራቅ ውስጥ በትራምፕ ትዕዛዝ በድሮን አማካኝነት በተፈፀመ ጥቃት መገደላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡ ጥቃቱ…

በተለያየ ጊዜ ሁለት ህፃናትን በማታለል ያደፈሩ ግለሰቦች ከ11 እስከ 25 ፅኑ እስራት ተቀጡ

በተለያዬ ጊዜ ሁለት ህፃናትን በማታለል የደፈሩ የ65 ዓመት አዛውንት በ25 ዓመት እንዲሁም ያሳደጋትን የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ገላን ጉራ አካባቢ በሚገኝ የአንድ…

የጠ/ሚ አረንጓዴ ዐሻራጥሪ በሚል መለያ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው ለሚያጋሩ አስደናቂ በረከቶች መዘጋጀታቸው ተገለፀ

በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የጠ/ሚ አረንጓዴ ዐሻራ ጥሪ በሚል መለያ ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ የፌስ…

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች “ጣናን እንታደግ” በሚል ወደ ባህርዳር ይሄዳሉ

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንደገለጹት በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት “ጣናን እንታደግ” በሚል ጣና ሃይቅን የወረረውን የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ወደ ባህርዳር ከተማ እንደሚጓዙ ተናግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ…

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ

በኢትዮጵያዊያን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተነሳሽነት የተጀመረው እና በርካታ አባላትን የያዘው ማህበር ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ ተመሰረተ። በአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የመገናኛ በዙሀን ድርጅቶች ባልደረቦች አባልነት የተቋቋመው ማህበሩ ዛሬ ሰኔ 18/2012 ምስረታውን በሚመለከት መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው በመገናኛ ብዙሃን ሙያና…

በ‹‹ማዕድ ማጋራት›› የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ መርሃ ግብር ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ሶልማክ አድቨርታይዚንግ ኤንድ ኤቨንትስ ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ሙዚቀኞች ህብረት ጋር በጋራ በመሆን ባካሔደው የጎዳና ላይ የሙዚቃ ዝግጅት ከ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ታወቀ። ዝግጅቱ በአይነቱ ለየት ያለ እና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዕለት ገቢያቸው ተጓድሎ በከፋ ችግር…

የጤና ሚኒስቴር በቀን 15000 ሰዎችን ለመመርመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

የጤና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 እለታዊ ምርመራን ወደ 15000 ከፍ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በአገራችን የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ሪፖረት ከተደረገበት ከመጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ ሰኔ…

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3,775 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ። በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4,848 ደርሷል። ዶክተር ሊያ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 47 ወንድና 138 ሴቶች…

የፌደራል መንግሥት የተከናውኑ ዓመታዊ ሥራዎችን በመገምገም ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህብራዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው ”ዛሬ በፌደራል መንግሥት የተከናውኑ ዓመታዊ ሥራዎችን የምንገመግምበት ዕለት ነው። ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ዕቅድ ማውጣት፣ የክንዋኔውን ሁኔታ ግብ ተኮር በሆነ፣ በቁጥር በሚለካ እና ሊመዘን በሚችል መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ አስታውቀዋል።  

በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ

በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል መከፈቱን የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት መሆኑም ተገልጿል። በማእከሉ የትኛውም ዜጋ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com