መዝገብ

Category: አንደበት

የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለፈው ሳምንታት ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ስም ዝርዝር ለፌደራል ፖሊስ መላኩ ይታወሳል። ሥማቸው የተላለፈው ባለሥልጣን ያለፉበትን ሂደት አስመልክቶ ከ አቶ መስፍን በላይነህ በፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ጋር ቆይታ አድርገናል። አቶ…

የ 2012 የአንደበት ትውስታ

2012 ዓመት አዲስነቱን ጀምሮ በአሮጌ መዝገብ ሰፍሮ እነሆ ተሸኝቷል። ባለፉት 365 ቀናት የነበሩትን ኹነቶችና በየጊዜው የሚሰሙ ክስተቶችን በመዘገብ የምትታወቀው አዲስ ማለዳም፣ ለተከታታይ 52 ሳምንታት በተለያዩ አምዶቿ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሳለች። ከእነዚህ አምዶች መካከል ‹አንደበት› በተሰኘውና የተለያዩ እንግዶቿን በምታስተናግድበት አውድም ከሃምሳ በላይ…

ቢያንስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአጠቃላይ ሕወሓት ይቅርታ መጠየቅ አለበት

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)ን ነቀምት ከተማ ገና የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያሉ፤ ከ41 ዓመታት ገደማ በፊት ነበር የተቀላቀሉት፤ ቀጀላ መርዳሳ። ያኔ የነበረው ትግሉ ወደ ሜዳ ሳይወርድ እና እንቅስቃሴው ከተማ ውስጥ በነበርበት ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መማክርት ጸሐፊ የነበረው…

በአዲስ ትውልድ የመጣው ኢሕአፓ

ኢሕአፓ በደርግ ዘመነ መንግሥት ብርቱ ‹ትግል› ያደርጉ ከነበሩ ፓርቲዎች መካከል ተጠቃሽና የማይረሳ ነው። ይህ ፓርቲ ታድያ ከኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ የተበተነ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ዓመት 2011 በስደት የቆዩት አባላቱ ተሰባስበው ዳግም ቀስቅሰውታል። ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘው ቴዎድሮሰ…

የተፋሰስ ልማት እና ነባራዊ እውነቶች

ኢትዮጵያ በውሃ ሀብት ሥሟ ቢነሳም በተጨባጭ የውሃ አያያዟና በሀብቷ የመጠቀሟ ነገር ከሥሟ የሚመጣጠን አይደለም። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያነቃው የውሃ ሀብት ጉዳይም ብዙዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ከማድረግ አልፎ ተቆርቋሪነት እንዲሰማቸው አድርጓል። የጣና በእንቦጭ መወረርም የተፋሰስ አካላት ያሉበት ሁኔታ እንዴት ነው ብሎ ለመጠይቅ…

የአዲሱ የትምህርት ዘመን እጣ ፈንታ በዘመነ ኮቪድ

ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ ለመገናኛ ብዙሃን በጣም ቅርብ የሆኑ ትሁት እና አንጋፋ የትምህርት ባለሙያ ናቸው።የልዩ ድጋፍ ትምህርት እና የትምህርት ሎሬት ሲሆኑ፣ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ላይ ላቅ ያለ ሙያዊ አበርክቶ እያደረጉ ያሉ ጉምቱ የዘርፉ ሊቅ ናቸው። በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ከፍተኛ…

በተግዳሮቶች መካከል ተስፋን ማስቀጠል

ዳረል ዊልሰን የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው። ባለፈው ዓመት በሹመት ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ጎረቤት አገር ኬንያ በናይሮቢ ቦትለርስ ለዘጠኝ ዓመታት አገልግለዋል። የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ የሆኑት ዳረል ዊልሰን፣ የለስላሳ መጠጥ ሥራን ለ27 ዓመታት ስለሚያውቁት በኢንዱስትሪው የካበተ…

ግብረ ሰዶማውያንን ከሚቃወሙ 10 አገራት መካከል ኢትዮጵያ የለችም

ወደኪስ የሚገባ ትርፍ አልያም የብዙኀንን አድናቆት፣ እውቅናና ጭብጨባ ለማግኘት ሳይሆን፣ ስለአገር በማሰብና በመጨነቅ ለትውልድም በመሳሳት እድሜ፣ ጊዜና ጉልበት እንዲሁም እውቀታቸውን የሚሰጡ ሰዎች ብዙ ናቸው ለማለት አያስደፍርም። እርሳቸው ታድያ ከጥቂቶቹ መካከል ይመደባሉ፣ መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ)። ላለፉት 25 ዓመታት የ‹ወይንዬ አቡነ…

ኢትዮጵያና አሐዱ ሬድዮ – በጥበቡ በለጠ አንደበት

‹የኢትዮጵያውያን ድምጽ› የሚለው ሐሳብ የተነሳበት ዓላማ እንዲሁም የሚደርስበት ግብ እንደሆነ ያስቀመጠ፣ ያለማቋረጥ ስለኢትዮጵያ በመሥራት የተጠመደ የሬድዮን ጣቢያ ነው፤ አሐዱ ሬድዮ። 94.3 ሜጋ ኸርዝ ላይ የሚገኘው ይህ ጣቢያ ላለፉት ሦስት ዓመታት አድማጮቹን ቤተሰብ እያለና ቤተሰብ አድርጎ የዘለቀ ሲሆን፣ በአጭር ጊዜም ብዙ…

ቁርጡ ያልተለየው የዓለም ምጣኔ ሀብትና አፍሪካ

በአፍሪካ እንደ አኅጉር አንድ ገበያ በመፍጠር ሂደትና ጥረት ውስጥ ሥማቸው ከሚነሳ ሰዎች መካከል ናቸው። አንድ ገበያ ለመፍጠርም የአፍሪካ ነጻ ገበያ ስምምነት እንዲኖር ለማስቻል በሚደረጉ ድርድሮች፣ የኢትዮጵያ ቀዳሚ ተጠቃሽ ባለሞያ እና ተደራዳሪም ናቸው። ሙሴ ምንዳዬ። በኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመልቲላተራል ንግድ…

ኢትዮጵያዊው የአረብኛ ቋንቋ ልሳን

ኢትዮጵያ በተለያዩ የውስጥ ጉዳዩቿ ተጠምዳ የምትገኝበት ጊዜ ነው። ከወቅታዊ አለመረጋጋቶች ባሻገር በግንባታ ሂደት የቆየውና የውሃ ሙሌት ሥራው ይጀመራል የተባለው የሕዳሴ ግድብ ጉዳይም በብዙዎች ሐሳብና ልብ ይመላለሳል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታድያ የግብጽ መገናኛ ብዙኀን የኢትዮጵያን ሥም የሚያነሱበትን መንገድና የሚያሰራጩትን ሐሰተኛና ትክክለኛ…

ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ የሠራተኞችን ደኅንነት ነው መጠበቅ ያለበት እንጂ ፈቃድ ውስጥ መግባት የለበትም

በኢትዮጵያ ከጥበቃ ሥራ ጋር በተገናኘ የሠራተኞችን ቅሬታ መስማት የተለመደ ነው። ይልቁንም ቃል ከተገባላቸው ደሞዝ በእኩል ያነሰ ደሞዝ ከማግኘትና ከሥራ ጫና መብዛትም ጋር በተገናኘ በተለይ የጥበቃ ሠራተኞች በማማረር ሲናገሩ ይሰማል። እንደ ኤጀንሲ ታይተን ባልተገኘንበት ተከሰናል የሚሉ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በአንጻሩ፣…

ኮቪድ 19 እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ

በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉና በወጣት እድሜ የሚገኙ፣ በአገሪቱ ጽንፍ የወጣ ነው ተብሎ በሚታማ ፖለቲካ ውስጥም በጎ ጎኖችን በማየት ለመልካም ውጤት ከሚሠሩ መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ሲያጠናቅቁ፣ ኹለተኛ ዲግሪያቸውን በዓለማቀፍ ፖሊሲ በአሜሪካ ከጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ሦስተኛ ዲግሪያቸውን…

ወረርሽኙን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት በቂ አይደለም!

ኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ከገባ ሦስት ወራትን ተሻግሯል። አካሄዱም እንደ አጀማመሩ አይደለም፣ ይልቁንም በየእለቱ በቫይረሱ መያዛቸው የሚረጋገጥ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ወደ ኹለት፣ ከኹለት ወደ ሦስት አሃዝ አድጓል። የጤና ስርዓቱ፣ የሕክምና ባለሞያዎች ሙያና አገልግሎት፣ መንግሥትና የመንግሥት ተቋማት በብዙ ተፈትነዋል።…

በማንኛውም ሁኔታ የግብርና እንቅስቃሴ መቋረጥ አይኖርበትም

በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንዲሁም በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ ላይ አደጋ በጣለውና አሁንም ስጋቱ ባልቀነሰው የበረሃ አንበጣ መንጋ ሰበብ የምሥራቅ አፍሪካ የምግብ ዋስትና ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። በአዘቦቱም ዜጎቿን በቅጡ መመገብ ያልሆነላት አፍሪካ፣ በዚህ ጊዜ ደግሞ የበለጠና ከባደ ፈተና ተጋርጦባታል። ወደፊትም…

የማንነት ፖለቲካ ሰብአዊ መብትን መጠቀሚያ ያደርጋል!

ከኹለት ዓመት ገደማ በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ የተመዘገቡ በርካታ ለውጦች አሉ። ይህም ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን መንግሥት ለተወሰነ ጊዜ አስመስግኖ ያቆየ ሲሆን፣ ብዙም ሳይቆይ ግን በተለይም ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ እዛም እዚም የሚሰሙ አሳሳቢ ጉዳዮች ተስተውለዋል።…

የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ታሪክን የኖሩት ባለሞያ

የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያን ከምሥረታው ጀምሮ ለ25 ዓመታት ከዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ፣ በኢንሹራንስ ዘርፍ ከ40 ዓመታት የዘለቀ ቆይታ አድርገዋል፤ ፀጋዬ ከምሲ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በንግሥ ሥራ ኮሌጅ ካገኙት ዲፕሎማ ባሻገር በመደበኛ ትምህርት የገፉ ባይሆንም፣ ዓመታትን በዘለቀው ልምዳቸው ግን ዘርፉን አንዳች…

በኢትዮጵያ በሚነሱ ግጭቶች ዋጋ የሚከፍሉት ቤተ እምነቶች ናቸው

ጅማ በ1999 ሃይማኖትን ሽፋን ባደረገ ግጭት ብዙ ዋጋ ተከፍሎባታል። ለበርካታ ዘመናት በፍቅር በኖረው ማኅበረሰብ ውስጥ በተነሳ በዚህ ግጭት ሳቢያ ቤተ እምነቶች ተቃጥለዋል፣ ምዕመናን ተገድለዋል። በዚህ ጊዜ ግጭቱ መነሻና አጀንዳው ሌላ፣ ሃይማኖትን ግን ሽፋንና መጠቀሚያ እንዳደረገ ለማኅበረሰቡ በማስረዳት ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት…

የግንቦት 7 አነጋጋሪ ጉዳዮች በኋሊት ቅኝት

በልጅነታቸው ከወላጅ አባታቸውና ከአባታቸው ጓደኞች አንደበት የሚወጡትን የፖለቲካ ወሬዎች ይሰሙ ነበር። ሻሸመኔ ‹ኩየራ› ልጅነታቸውን ያሳለፉት ኤፍሬም ማዴቦ፣ ሐዋሳ ከተማ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተከታትለዋል። ቀጥሎ በመጣላቸው ነጻ የትምህርት እድል ባቀኑበት ደብረዘይት ኢቫንጀሊካል ትምህርት ቤት፣ ከ14ቱም ክፍለ አገር የመጡ ተማሪዎች ነበሩ። ያኔ…

ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካ የለም

መስፍን ወልደማርያም (ፕሮፌሰር) የአደባባይ ምሁር ተብለው ከሚጠሩ ጥቂት ምሁራን መካከል በግንባር ቀደምትነት ሥማቸው ይጠራል። ብዙ ወዳጆቻቸው የኔታ የሚሏቸው ፕሮፌሰር መስፍን፣ 90ኛ የልደት በዓላቸውን ትላንትና አርብ፣ ሚያዚያ 16/2012 አክብረዋል። የኔታ መስፍን በረጅሙ የዕድሜ ዘመናቸው ሙያቸውን በተመለከተ እንዲሁም ያገባኛል ይመለከተኛል በሚሉት ማንኛውም…

‹‹ሰው እያየ ከሚደረገው፣ ተደብቆ የሚደረገው መልካም ነገር ይበልጣል››

1441ኛው የረመዳን ጾም ተጀምሯል። በእስልምና ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣው አጽዋማት መካከል ቀዳሚው ነው። ታድያ የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተንሰራፋበት በዚህ ጊዜ ጾሙን በተመለደ ስርዓት ማከናወን ከባድ ነው። ሕዝበ ሙስሊሙም ከወዲሁ ወደ መስጊድ ከመሄድ ታቅቦ በየቤቱ ሆኖ ጸሎቱንና ስግደቱን በማድረስ ላይ…

“ሃይማኖት በሰዎች ድካም፣ ስቃይና መከራ ውስጥ ትርጉም ይፈልጋል።”

ከሃምሳ አምስት ቀናት የጾም ቆይታ በኋላ የሚመጣውና በክርስትና እምነት በድምቀት የሚከበረው የትንሣኤ በዓል ዘንድሮ እንደቀደሙት ዓመታት በጥብቅ ቤተሰባዊና ማኅበራዊ መስተጋብር አይከበርም። ይህ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓሉን በሚያከብሩ የዓለም አገራት ዘንድም የታየ ነው። ከበዓሉ ቀድሞ የሚገኘውን ስቅለት እንዲሁም ሰሞነ ሕማማትን የክርስትና…

‹‹በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 35 ማስፈጸሚያ ደንብና መመሪያ ሊቀመጥ ይገባል››

የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ከማስጨነቁ በላይ የተለያዩ አሳሳቢ ክስተቶችንም እያስከተለ ነው። ከዚህም መካከል አንደኛው ቫይረሱን ለመቆጣጠር እንዲያስችል ቤት ውስጥ መቀመጥ አማራጭ መሆኑ፣ የቤት ውስጥ ጥቃትን እንዲጠነክር ማድረጉ የሚታወስ ነው። ይህም አሁን ላይ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆኗል። በኢትዮጵያም…

የኮሮና ወረርሽኝ እና የሥነ ልቦና ጫናው

ረዳት ፕሮፌሰር ማጂ ኃይለማርያም በሥነ አዕምሮ ጤና ኤፒዲሞሎጂ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን የማስተርስ ዲግሪያቸውንም በሶሻል ወርክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል። ማጂ ኃይለማርያም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን አገር ሚችጋን ግዛት በሚችጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ ውስጥ የፖስት ዶክቶራል ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ በዛው ዩኒቨርስቲ ውስጥ…

‹‹የፌዴራል መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሲያውጅ የክልሎችን ሥልጣን ጭምር ማገድ ይችላል››

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ላይ መንግሥት መደበኛውን ስርአት ተጠቅሞ ሕግ ማስከበር የማይችል ሲሆን፣ ከተወሰኑ መብቶች ውጪ መብቶችን እንዲገድብ ሥልጣን የሚሰጥበት ሂደት ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ያለ ከሆነ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በታወጀ በ48…

‹‹አሠራሩ ካልዘመነ፣ ኤጀንሲው ባለው አቅም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መከታተል ይከብደዋል››

የከፍተኛ ትምህርት ጥራት እና አግባብነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) አሁን ላይ የሚገኙበትን የሥራ ኃላፊነት ከመያዘቸው በፊት ኢትዮ ቴሌኮምን ከ2005 እስከ 2010 ድረስ መርተዋል። እንዲሁም በተቋሙ የኦዲት እና የሰው ሀብት መኮንን በመሆንም አገልግለዋል። አንዱዓለም የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ዲግሪያቸውን…

‹‹የእርሻ መሬት ሊስፋፋ የሚችልበት ቦታ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም››

ትውልዳቸው ናዝሬት ከተማ ነው፤ የ80 ዓመቱ አዛውንት ደሳለኝ ራኽመቶ። ከመሬት ጋር በተገናኙ ጉዳዩች ሐሳብና አስተያየት እንዲሰጡ ቀድመው ሊጠሩ ከሚችሉና በጉዳዩም የበሰለ እውቀትና መረጃ ካላቸው ሰዎች መካከል ናቸው። አብዛኛውን እድሜያቸውን ለጉዳዩ ሰጥተው የተለያዩና ሰፋፊ ጥናቶችን በግብርናው ዘርፍ አካሂደዋልና የመሬት ጉዳይ ከእግር…

‹‹የሚያጣላን የፖለቲካ ታሪክ ሳይሆን የታሪክ ፖለቲካ ነው››

ትውልድና እድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ዘርፈሽዋል እንዲሁም ገዳመ ሲታውያን ማርያም ጽን ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ኹለተኛ ደረጃ ደግሞ ምሥራቅ አጠቃላይ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በታክ የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ዲግሪያቸውን ይዘዋል። በዲላ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም በአወልያ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት…

ከአማራ ያለፈ ሕዝባዊ ተቀባይነት የሚማትረው አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ልክ የዛሬ ሳምንት ነበር፣ በካሄደው ምርጫ የቀድሞ ሊቀመንበር የነበሩትን ደሳለኝ ጫኔን (ዶ/ር) በበለጠ ሞላ የተካው። ከዚህም ባሻገር የተለያዩ መዋቅራዊ ለውጦችን አካሂዷል። ከምክትል ሊቀመንበርነት አንድ ደረጃ ከፍ በማለት ፓርቲውን በመሪነት የተረከቡት በለጠ፣ ፓርቲውን ከመጪውን አገራዊ ምርጫ ፈተና…

‹‹አሁን ኢትዮጵያ ካለፈው የባሰ የሰብአዊ መብት ጥሰት ውስጥ ነች ብዬ አላምንም››

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ነበር ያገኙት። ቀጥለውም በ‹ዴቨሎፕመንት ስተዲስ› ኹለተኛ ዲግሪያቸውን ይዘዋል። በዚህ አላበቁም፣ ከኢንግሊዙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለም አቀፍና ሰብአዊ መብቶች ሕግ ኹለተኛ ዲግሪ፣ በዓለም አቀፍ ሕግ ደግሞ ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በመሥራት የዶክትሬት ማዕረግ ጭነዋል፤ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)። ዳንኤል…

This site is protected by wp-copyrightpro.com