የእለት ዜና
መዝገብ

Category: ዜና

ባንኮች ሠራተኛ ለመቅጠር ገንዘብ እየጠየቁ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብዙ ባንኮች ሠራተኞችን ለመቅጠር ገንዘብ እንደሚጠይቁ ተመርቀው ሥራ የሚፈልጉ ወጣቶች ለአዲስ ማለዳ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። አንዳንዴ የሥራ ማስታወቂያው ከወጣ በኋላ ማን እንደሚገባበት አይታወቅም ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ የተወሰኑ ባንኮች ላይ እስከ 50 ሺሕ ብር ከፍለው የገቡ የምናውቃቸው ሥራ ፈላጊዎች አሉ…

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በድንጋይ ከሰል ዕጥረት ምክንያት ችግር ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ

በአገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ዕጥረት እና ጥራት መጉደል ምክንያት የማምረት አቅማቸው እየተዳከመ እንደሚገኝ ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች ገለጹ። መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከውጪ በተለይም ከደቡብ አፍሪካ እና ሩሲያ ይገባ የነበረውን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በማሰብ በአሁኑ ጊዜ ወደ 68…

ለድንበር ላይ ንግድ ሕጋዊ አሠራር ይፈጥራል የተባለለት ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ

ለድንበር ላይ ንግድ ሕጋዊ አሠራር ይፈጥራል የተባለለት ረቂቅ መመሪያ በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የባለድርሻ አካላትን አስተያየት እየጠበቀ እንደሆነ ተገለጸ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም በአግባቡ የተሰነደ ሕጋዊ ማዕቀፍ እና ቅርጽ የሌለውን የድንበር ላይ ንግድን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር…

በቦረና ዞን በዝናብ ዕጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተገለጸ

የቦረና ዞን ነዋሪዎች በዝናብ ዕጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ ለውኃ፣ለምግብና ለጤና ችግር መጋለጣቸው ነው የተነገረው። ድርቁ የተከሰተው በዞኑ በ2013 የበልግ ዝናብ በቂ ባለመሆኑና የ2014 የመኸር ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት እንደሆነ ነው የተገለጸው። በድርቁ የተነሳም በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ የተነገረ…

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአልባሳት ማምረት ዘርፍ የ30 ዓመታት ልምድ ካለው የግሪክ ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት ማካሄዱን አስታውቀ

የውል ስምምነቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና በዲሚትሪየስ ካምፑሪስ (ካምቦቴስ) ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲሚትሪየስ መካከል እንደተደረገ ተገልጿል። በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ድርጅቱ ያቀረበው የለማ መሬት ጥያቄ በኮርፖሬሽኑ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ በ15 ወራት ውስጥ የግንባታ ሥራዎችን…

መፍትሔ ያልተቸረው የጦርነቱ ቀጠና

አፈወርቅ እንዳየሁ በአማራ ክልል መቄት ወረዳ ሸደሆ መቄት ሆስፒታል በፋይናንስ ሥራ አገልግሎት እየሰጡ የቆዩ ናቸው። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት አካባቢውን ከተቆጣጠረበት ከሐምሌ ማገባደጃ 2013 ጀምሮ በአካባቢው ነዋሪዎችና በራሳቸው ላይ የደረሰባቸውን ድርጊት በምሬት ያስታውሳሉ። ግለሰቡ እስካሁን መንግሥት…

የአዲስ አበባን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቆጣጠር ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ መሠራት አለበት ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቆጣጠር በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ መኪኖች በብዛት መኖራቸው፣ እንዲሁም ከሕዝብ ፍሰቱ እና ከነዋሪው ፍላጎት ጋር ተያይዞ በየጊዜው የተሸከርካሪ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በከተማዋ አየር ንብረት…

መንገደኞችን የሚያማርሩ የትራንስፖርት ውስብስብ ችግሮች

በመዲናዋ አዲስ አበባ የነዋሪዎች ፈተና ከሆኑ ብዙ ነገሮቸ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የትራንስፖርት ችግር ነው። ከቤት እንደወጡ የፈለጉትን የትራንስፖርት አማራጭ ማግኘት መቻል ቀላል አይደለም። ጊዜን እና ገንዘብን አላግባብ ከሚያባክኑ የነዋሪው ፈተናዎች ውስጥ የትራንሰፖርት ችግር በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው። ይህም በየጊዜው…

ተወርቶ የሚረሳው የወለጋ የዜጎች ሰቆቃ

በኢትዮጵያ የዜጎች ግድያ፣መፈናቀል እና በረሀብ አለንጋ መገረፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ መቋጫ እያጣና እየተባባሰ መጥቷል። በኦሮሚያ ክልል ወለጋ የተለያዩ ዞኖች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የሚደርሰዉ ሰቆቃ እጅግ እየከፋ መምጣቱ የአደባባይ ምስጢር ሆኗል። ግድያዉ አየተባባሰ የመጣዉ ከጥቅምት 2013 ጀምሮ…

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቆዳ 10.3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

በ2014 በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቆዳና የቆዳ ምርቶች 10 ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ባለፈው መስከረም 30 በተጠናቀቀው የ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከውጭ ገበያ…

ሕወሓት ከ300 በላይ መኪናዎች አዘጋጅቶ በውርጌሳና ውጫሌ ያሉ ንብረቶችን “ዘርፏል” ተባለ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል በሽብርተኛነት የተፈረጀው ህወሓት ከ300 በላይ ተሳቢ መኪናዎችን አዘጋጅቶ በደላንታ፣ ውርጌሳና ውጫሌ አካባቢ ያሉ የመንግሥትና የበርካታ ግለሰቦችን ንብረት “መዝረፉን” የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። የአዲስ ማለዳ ምንጮች የተናገሩት፣ ባሳለፍነው ሳምንት (ጥቅምት 2014 ኹለተኛ ሳምንት) ሽብርተኛ የተባለው…

ኮሜርሻል ኖሚኒስ የጉልበት ብዝበዛ እያደረሰብን ነው ሲሉ ሠራተኞቹ ተናገሩ

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በሠራተኞቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ በደልና የጉልበት ብዝበዛ፣ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሰ ይገኛል ሲሉ መሠረታዊ የሠራተኞች ማኅበር አባላት ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የሠራተኞች ማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አብርሃም አድኖን ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ አሁን ላይ ኮሜርሻል…

የዶሮ እና እንስሳት ሀብት ላይ ያተኮረ ዓውደ-ርዕይ ሊካሄድ ነው

29ኛው የኢትዮጵያ እንስሳት ዕርባታ ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤ፣ 10ኛው የኢትዮ ፓልተሪ ኤክስፖና 6ኛው የአፍሪካ እንስሳት ዓውደ-ርዕይ እና ጉባኤ ከፊታችን ከጥቅምት 18 እስከ 20 በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል፣ እንዲሁም ከጥቅምት 22 እስከ ኅዳር 22/2014 ድረስ በበይነ-መረብ እንደሚካሄድ ተገለጸ። ዓውደ- ርዕዩና…

በጦርነቱ ቀጠና ውስጥ በምትገኘው ወልድያ ከተማ የአተት በሽታ መከሰቱ ተሰማ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በጦርነቱ ቀጠና ውስጥ በምትገኘው የወልድያ ከተማ የአተት (አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት) በሽታ እንደተጋረጠባቸው ባሳለፍነው ጥቅምት 8/ 2014 ወደ አዲስ አበባ የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። “ቤታችንን ለቀን ወዴት መሄድ እንችላለን?” ብለው በጦርነቱ የሚደርስባቸውን ችግር ተቋቋመው…

በሱማሌ ክልል ዕድሜያቸው ለምርጫ ያልደረሰ ሕፃናት ድምጽ ሰጥተዋል ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው መስከረም 20/2014 ባካሄደው ኹለተኛው ዙር ምርጫ በተለይ በሱማሌ ክልል ዕድሜያቸው ለምርጫ ያልደረሰ ሕፃናት ድምጽ መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ። መስከረም 20 በክልሉ በተካሄደው ምርጫ በታዛቢነት የተሳተፈው ኢሰመጉ፣ በክልሉ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ዕድሜያቸው ለመምረጥ…

እስክንድር ነጋ በማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ ተፈጸመበት

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስሮ የሚገኘው እስክንድር ነጋ ጥቅምት 11 ቀን ንጋት ላይ እንደተለመደው ከሌሎች እስረኞች ጋር ሆኖ ስፖርት በመሥራት ላይ እንዳለ በኹለት እስረኞች ድብደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው የሆኑት ሔኖክ አክሊሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ኹለቱ እስረኞች አስቀድመው ከእነእስክንድር ጋር በቂሊንጦ ታስረው የነበረ…

‹ኮላብ ሲስተምስ› በ‹ኢግል ሒልስ› ክህደት ተፈጽሞብኛል ሲል አስታወቀ

ድሮም ዘንድሮም የሚባል የቀደምት (ክላሲክ) መኪናዎች ትዕይንት በማዘጋጀት የሚታወቀው ኮላብ ሲስተምስ ድርጅት፣ በለገሀር ባቡር ጣቢያ ከኢግል ሒልስ ጋር በአጋርነት ሊያዘጋጀው የነበረውን የመኪና ትዕይንት እንዳይካሄድ በማድረግ ኢግል ሒልስ ክህደት ፈጽሞብኛል ሲል ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል። በኮላብ ሲስተምስ ውስጥ በኃላፊነት ተመድበው የሚሰሩ እና…

በወተትና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያዎች ላይ አስገዳጅ ደረጃዎች ጸደቁ

የሽሮ፣ በርበሬ፣ ቆሎ፣ በሶ፣ ጠጅ እና አረቄ አስገዳጅ ደረጃዎችም ለመጀመሪያ ጊዜ በምክር ቤቱ ቀርበው ጸድቀዋል

ፑራቶስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በ120 ሚሊዮን ብር የፈጠራ ማዕከል መገንባቱን አስታወቀ

ፑራቶስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የዳቦ፣ የኬክና የቸኮሌት ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካና ልዩ የምግብ ፈጠራ ማዕከል ግንበቶያስመረቀ ሲሆን፣ ለፈጠራ ማዕከሉ ግብታ 120 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አጠቃላይ ፋባሪካውን እና ማዕከሉን ለማስገንባት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ፑራቶስ ኢትዮጵያ መሰረቱን ቤልጂየም ያደረገው…

የንግድ ትርዒት – የአዳዲስ እድሎች አውድ

ዓለማችን የግብይትና የንግድ ትስስር መንገዶችን በየጊዜው በማሻሻል አዳዲስ መንገዶችና አካሄዶችን በተለያየ ጊዜ አስተናግዳለች። በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሁም በአካል ሰዎች የሚገናኙባቸው መድረኮችም በተለያየ ጊዜ ተፈጥረው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ከዚህ መካከል አንደኛው የንግድ ትርዒት ነው። አገራት በየዘረፉ ለተለያዩ ዓላማዎች የንግድ ትርዒቶችን ያስተናግዳሉ፤ ያካሂዳሉ።…

ለዕርዳታ የሚውል 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን መጠባበቂያ እህል ግዢ መፈጸሙ ተነገረ

የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የመጠባበቂያ እህል ግዢ መፈጸሙን ተናግሯል። በአገሪቱ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ምግብ የሚውል መጠባበቂያ እህል በ8 ማዕከላዊ መጋዝኖች ውስጥ ይገኛል…

በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ሲያስተምሩ ለነበሩ ተፈናቃይ መምህራን ደሞዝ መክፈል ተጀመረ

ደሞዛቸው ተቋርጦባቸው የነበሩ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስዎች ውስጥ ሲያስተምሩ ከነበሩ መምህራን መካከል፣ የራያ እና መቐለ ዩኒቨርስቲ መምህራን ደሞዝ አንደተከፈላቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች መምህራን ላለፉት ኹለትና ከዚያበላይ ለሆኑ ወራት ደሞዝ እየተከፈላቸው…

ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ሰሊጥ ወቅቱን ባለጠበቀ ዝናብ እንዳይጎዳ እየተሰበሰበ ነው ተባለ

በምዕራብ ጎንደር ዞን በ130 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ የለማ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ሰሊጥ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይጎዳ መሰብሰብ መጀመሩን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በ2013/14 ምርት ዘመን በባለሃብቶችና አርሶ አደሮች ከዘመቻ ጎን ለጎን የለማ የሰሊጥ ምርት እየተሰበሰበ ነው ያለው ግብርና መምሪያው፣…

“ጤና ዘይት” የማምረት አቅሙን 130 በመቶ ማሳደግ የሚያስችለውን ምርት መጀመሩን አስታወቀ

የምግብ ዘይት የሆነው ጤና የሱፍ ዘይት፣ በዱከም ከተማ የፋብሪካ ማስፋፊያ የጀመረ መሆኑን የምርቱ ባለቤት ‹‹54 ካፒታል›› የተሰኘው ድርጅት ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል። ይህን ተከትሎም አሁን ላይ ከኹለት ዓመት በፊት የተጀመረው የማስፋፊያው የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው 130 በመቶው ተጠናቆ ምርት መሥጠት መጀመሩን ነው…

በአንድ ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባ የተገነባው “ኃይሌ ግራንድ” ሆቴል ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው

በአንድ ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባ የተገነባው ኃይሌ ግራንድ የተሰኘ የሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ የካ ክፍለ…

ከሞት ያላዳነ የንጹኃን ዜጎች የድረሱልን ጩኸት

ሰይድ አደም ይባላል። ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን መንደር አራት ቀበሌ ነው። ሰይድ በንግድ ሥራ የሚንቀሳቀስ ታታሪ ወጣት ሲሆን፡ በኦሮሚያ ክልል ይወለድ እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ክልሎች በተደጋጋሚ ሲዘዋወር እንደኖረ ያወሳል። ከዓመታት ወዲህ ግን ነገሮች መልካቸውን…

የተራዘመ ጦርነት እና የተባባሰው የሕዝብ ችግር

መነሻውን በትግራይ ክልል ያደረገው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ጦርነት፣ ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው 18 ቀናት ይቀሩታል። ጦርነቱ የተጀመረው ጥቅምት 24/2013 በትግራይ ክልል ይሁን እንጅ ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ የትግራይ አጎራባች ወደሆኑት አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቷል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…

በ22 ከተሞች የ‹4ጂ ኤል.ቲ.ኢ› ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ተጀመረ

በኹለተኛ ዙር ማሥፋፊያ ሥራው በ22 ከተሞች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሩን ኢትዮ-ቴሌኮም ይፋ አድርጓል። በመጀመሪያው ዙር የማስፋፊያ ሥራው ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 92 ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አስጀምሮ የነበረው ኢትዮ-ቴሌኮም፣ በኹለተኛው ዙር የ4ጂ…

ባህርዳር በሚገኘው ዘንዘልማ የተፈናቃዮች መጠለያ የፊት ቁስለት በሽታ መከሰቱ ተገለጸ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት በተፈረጀው ህወሓት ጥቃት ከአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን ተፈናቅለው በባህርዳር ዘንዘልማ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች የፊት ቁስለት በሽታ እንዳጋጠማቸው ገለጹ። ህወሓት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ከጥቃት ሸሽተው ባህርዳር በሚገኘው ዘንዘልማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ምንነቱ…

ቤተሰቦቻቸው በጦርነት አካባቢ የሚገኙ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ችግር ላይ ነን አሉ

ከግቢ ውጡ የተባሉ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ያሉበት አካባቢ በጦርነት ቀጠና ውስጥ በመሆኑ ማረፊያ ስለሌላቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ዩኒቨርሲቲው አገራችን ያለችበትን ጦርነት ግምት ውስጥ በማስገባት የ2013 ትምህርት ዘመን ተመራቂዎችንና የኹለተኛ ዓመት ተማሪዎችን የተለመደውን የአልጋና የምግብ አገልግሎት እያገኙ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com