የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አዲስ መጽሃፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

0
586

ሐምሌ 10 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹የትርክት እዳና በረከት›› በሚል እርዕስ አዲስ መጽሃፍ ለንባብ ሊያበቁ መሆኑን አዲስ ማለዳ የደረሳት መረጃ ያመላክታል፡፡

በገዢው ፓርቲ የስልጣን መዋቅር ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ በአንድ በኩል የበዛ ትችትን በሌላኛው ጫፍ ደግሞ ድጋፍን እያስተናገዱ ያሉት ዲያቆን ዳንኤል ከአሁን ቀደም በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በጸፏቸው መጽሃፍቶችና በሚሰጧቸው ትችቶች ይታወቃሉ፡፡

አዲሱ መጽሃፋቸውም በተለይም በአሁን ወቅት ዋነኛ የአገሪቱ የፖለቲካ ህመም ሆኖ የሚነሳው የትርክት ጉዳይ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ስለመጻፉም ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

አማካሪው በአማራ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎችን ‹‹ጃዊሳ ››በሚል ስም መጥራታቸውን ተከትሎም በአንድ ወቅት መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በሚሰጧቸው አነጋጋሪና አጨቃጫቂ አስተያየታቸው የሚታወቁት ዲያቆን ዳንኤል በኦሮሞ ልሂቃን ዘንድም በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን ስልጣን ይነጠቁ ዘንድ ግፊት ሲደረግባቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ባለፈው ምርጫ በአዲስ አበባ ብቸኛ የግል ተወዳዳሪ ሆነው በመቅረብ የፓርላማ ወንበርን ያገኙ ሲሆን ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here