ለቀናት ታግተው የነበሩ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ሰራተኞች ተለቀቁ

0
668

👉 ፋብሪካው ለሁለት ቀናት ስራ አቁሞ እንደነበር ተገልጿል

ሐምሌ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በማእከላዊ ጎንደር ዞን ልዩ ቦታው ቆላድባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በውሃ ማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት የፋብሪካው ሰራተኞች ናቸው መለቀቃቸው የተነገረው፡፡

እገታው ተፈጸመ የተባለው በፋኖ ሃይሎች ሲሆን የሰራተኞቹን መታገት ተከትሎም ፋብሪካው ለሁለት ቀናት ስራ አቁሞ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ታጣቂዎቹ ዛሬ ጠዋት ሁለቱን ሰራተኞች የለቀቁ ቢሆንም ሰራተኞቹ ሲገለገሉባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች ግን አለመመለሳቸውን ለአዲስ ማለዳ የደረሳት መረጃ ይጠቁማል፡፡

የሰራተኞቹን እገታ ተከትሎም በፋብሪካው ያሉ ሰራተኞች ወደ አካባቢው አቅንተው ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳም የምርት መቋረጥ ለቀናት አጋጥሞ እንደነበረ ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

በጉዳዩ ላይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ሃይሎችም ሆነ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ አመራሮች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ ያሉት ነገር የለም፡፡

ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ እገታዎችንና አፈናዎችን በተመለከተ የፋኖ ታጣቂዎች በተደጋጋገሚ ማስተባቢያዎችን ሲሰጡ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here