በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትጵያዊያን ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

0
310

ማክሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በሊባኖስ እየተባባሰ ከመጣው የጸጥታ ችግርና ውጥረት ጋር ተያይዞ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት አሳስቧል፡፡

በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ዜጎች ከቆንስላውም ሆነ ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚወጡ መረጃዎችን በንቃት እንዲከታተሉ፤የአገሪቱ መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎች እንዲያከብሩ፣ በሰልፎችና ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ከመገኘት እንዲርቁ ሲልም የቆንስላ ቢሮ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

ከቀናት በፊት በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በሊባኖስ ያለውን የዜጎቻችን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልን ነው ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

ዜጎችን ወደ አገር ለመመለስም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉም ነበር በመግለጫቸው ያብራሩት፡፡

የሂዝቦላ ቁልፍ ወታደራዊ አዛዥ የነበረው ታሊብ አብደላ በእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት መገደሉን ተከትሎ በሊባኖስና በቀጠናው አገራት ከፍተኛ ውጥረት እንደነገሰ የሚታወቅ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here