ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ በተከሰተው ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር ምክንያት አብዛኛዎቹን በረራዎች ወደሌላ አየር ማረፊያዎች እያዛወረ እንደሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።
ይህ በጠዋት የሚከናወኑ የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ በረራዎች ላይ ተፅእኖ አሳድሯል ያለው አየር መንገዱ ይሁንና በተጓዦች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ መጉላላቶችን ለመቀነስ ስራዎችን እየሰራን ነው ብሏል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጓዦች ላይ ለደረሱ መጉላላቶችም አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል።


