“የመምህራኑ መሰረታዊ ፍላጎት ሳይሟላ ስልጠና መስጠት በጊዜ መቀለድ ነው”- መምህራን

0
841

ዓርብ ነሐሴ 17 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ለቀናት ሲሰጥ የቆየው የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ አቅም ግንባታ መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በስልጠናውም መምህራን በሚያስተምሩበት የትምህርት አይነት፣ የማስተማር ስነ-ዘዴ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ላይ ብቃታቸውን ለማሻሻላል ታሳቢ ተደርጎ ለመምህራን ስልጠና መሰጠቱ ተጠቁሟል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ስልጠናው በ28 ዩኒቨርስቲዎች ሲሰጥ የቆየ ሞሆኑን ገልጸው 49 ሺህ 505 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች፣ 2ሺህ 892 አሰልጣኞች እንዲሁም 224 ዋና አሰልጣኞች እንደተሳተፉበት ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ መምህራኑ ምንም የተመቻቸ ሁኔታ ባልተሟላበት በዩንቨርስቲዎች እንድንሰለጥን የተገደድንበት ሁኔታ አግባብነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡

ለተከታታይ 24 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በየትምህርት ቤቱ በፕላዝማ ቢበዛ በ5 ቀን ስልጠናውን እንዲከታተል ቢደረግ ተገቢ ሆኖ ሳለ በብዙ ነገር በስነልቦና እንዲሁም በኢኮኖሚ የተጎዳን መምህር ለቀናት መንገላታታቸውን ገልጸዋል፡፡

መምህራን አሁን ባሉበት የደሞዝ ጭማሬ ጥያቄ እና የኢኮኖሚ ችግር ላይ ስልጠናው ያለ አበል መሰጠቱ ችግሩን እንዳባባሰው አመላክተዋል፡፡

እንዲሁም ዓላማው ግልፅ ባልሆነ መንገድ ከ2ዓመት የመጀመሪያ ድግሪ እሰከ 35 ዓመት የ2ኛ ድግሪ መምህራን በአንድ ቋት ስልጠና መስጠት ምንን የሚያመላክት ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በሃገር ደረጃ የሚደረገው የደሞዝ ማሻሻያ የመምህራንን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንዲስተካከል እንፈልጋለን ሲል የኢትዮጲያ መምህራን ማህበር ማስታወቁን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሺመልስ አበበ ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምንም እንኳን የደሞዝ ማሻሻያው ገና ተሰርቶ ያላለቀና በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያልጸደቀ ቢሆንም ማህበሩ የተሻለ የደሞዝ ጭማሪ ለመምህራን ይደረጋል የሚል እምነት እንዳለው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here