ፒያሳ የሚገኘው የመብራት ሀይል ህንፃ የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ በካሬ 19ሺ ብር መቅረቡ ተሰማ

0
497

ዓርብ ነሐሴ 17ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ፒያሳ የሚገኘው የመብራት ሀይል ህንፃ ለንግድ ቤቶች ኪራይ ጨረታ መቅረቡን ተከትሎ በካሬ 19ሺ ብር እየተጫረተ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ይህ የብር ተመን የቀረበው 40 ካሬ ላለዉ ምድር ላይ ለሚገኘው የንግድ ቤት ሲሆን አሸናፊው ቫት እና የጋራ ወለል ኪራይን ሳይጨምር በወር 760 ሺ ብር ይከፍላልም ተብሏል ።

በዚህ ወለል ላይ በካሬ 16 ሺ እና 15 ሺ ብር ያቀረቡ ሲኖሩ ከመቶ በላይ የንግድ ሱቆች ለኪራይ ጨረታ በዚህ ህንፃ ላይ መቅረባቸው ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለው የልማት ፕሮጀክት የፒያሳ ኮሪደር ልማት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከነበረበት ሕንፃ በመነሳት ወደሌላ ቦታ መግባቱን ተከትሎ ለንግድ ቦታዎች ክፍት መደረጉ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ከአካባቢው የተነሱ ወርቅ ቤቶችና ሌሎች የንግድ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም ህብረተሰቡ እነዚህን አገልግሎቶች እንዳያጣ የሚመጥን መሰረተ ልማትና አገልግሎት እንዲኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መልቀቁ ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here