አቶ ጌታቸው የስልጣን ሽምሹር ማድረጋቸው ተሰማ

0
1047

ቅዳሜ ነሐሴ18 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ጊዚያዊ አስተደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ሾመዋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ  ፀጋይ ገብረተኽለ የዞኑ አስተዳዳሪ በመሆን ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አደራ ሲል አሳስቧል።

አዲሱ ተሿሚ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ ቀደም ሲል በዞኑ የእንደርታ ወረዳ አስተዳዳሪ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው የስልጣን ሹምሽር ያደረጉበት የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተሸሙት ወ/ሮ ሊያ ካሳ የተኩት አምስተኛ የእነ ደብረፂዮን አካሄድ የሚቃወሙ የዞን አስተዳዳሪ ናቸው።

ለሁለት ተከፍሎ ውዝግብ ውስጥ የገባው ህወሃት አባላቱ ጉባኤ ማካሄድ አለብን ወይስ የለብንም የሚለው ፖለቲካዊ ክርክራቸው ከፍ ብሎ  ቀጥተኛ ወደሆነ የስልጣን ሽሚያ ውስጥ እንደገቡ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አሁን ላይ በህወሃት ውስጥ ውክልና ስለሌለው ጊዚያዊ አስተዳደሩን የመምራት አግባብነት የለውም በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር መወያየት ያስፈልጋል ያሉ ቢሆንም ህወሃት የራሱን ሰዎች በጊዚያዊ አስተዳደር ውስጥ ለመመደብ የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም ሲሉ የህወሃት ሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መናገራቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here