ተፈናቃዮችን በቋሚነት የማቋቋም ሥራ ከዕቅድ በዘለለ ወደ ትግበራ አልገባም -ኢሰመኮ

0
285

ሰኞ ነሐሴ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኦሞ ወንዝ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ከነሐሴ ወር የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ በሆነው የኦሞራቴ ከተማ እንዲሁም ቻይና ካምፕ በተባሉ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ በውሃ የመጥለቅለቅ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል ብሏል።

ኢሰመኮ አደረኩት ባለው ክትትል በባዩ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ 2 ሺህ 744 የሚሆኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በአካባቢው በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ለዳግም መፈናቀል መዳረጋቸውን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በስፍራው በተከሰተው የውሃ መጥለቅለቅ ከኦሞራቴ ወደ ነብረሙስ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ በመሰንጠቁ ምክንያት ለከባድ ጭነት ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሥጋት በመፍጠሩ እና ለተፈናቃዮች በሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ መስተጓጎልን ማስከተሉ የተፈናቃዮቹን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አሳሳቢ ማድረጉ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ለተፈናቃዮች ሲቀርብ የነበረው የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በመቋረጡ ተፈናቃዮች ንጽሕናው ያልተጠበቀ ውሃ ከኦሞ ወንዝ በመቅዳት እየተጠቀሙ መሆኑን ኮኒሽኑ ገልጻል፡፡

ተፈናቃዮች የሚኖሩባቸው መጠለያ ጣቢያዎች በጎርፍ ውሃ የተከበቡ በመሆናቸው ለወባ በሽታ መጋለጣቸውን፤ የንጹሕ ውሃ አቅርቦት እና በቂ የመጸዳጃ አገልግሎት ባለመኖሩ በአካባቢው የኮሌራ በሽታ ሥጋት ቢኖርም የወባ በሽታ መድኃኒት እና የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር አቅርቦት እጥረት መኖሩ ጠቁሟል።

አብዛኞቹ ሰዎች ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በመፈናቀል ሁኔታ ውስጥ ሲኖሩ የነበረ ቢሆንም ተፈናቃዮቹን በቋሚነት የማቋቋም ሥራዎች ከዕቅድ በዘለለ ወደ ትግበራ አልተገባም ሲል ኮሚሽኑ ገልጻል።

በመሆኑም ከደቡብ ኦሞ ዞን እና የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት አፋጣኝ እርምጃ የሚፈልጉ ሁኔታዎች ማለትም፤ የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት፣ የወባ በሽታ መድኃኒት፣ የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር እና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here