የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ሊያቋርጥ መሆኑን ገለጸ

0
207

ሰኞ ነሐሴ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ሊያቋርጥ መሆኑን አስታውቋል።

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ እንዲጨምር እንዲሁም የሚጠቀምበትን አውሮፕላን አይነት ከፍ ባሉት እንዲቀይር ከወራት በፊት አሳስቦ ነበር።

“ይህ ብቻ አይደለም፣ አዳዲስ ምክንያቶችም መኖራቸውን የገለጸው አየር መንገዱ ከኤርትራ በኩል አየር መንገዱ ላይ የሚደረገው ጫና መጠኑ ከፍተኛ ሆኗል” ማለቱ ተሰምቷል።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ ደብዳቤና ፈቃድ ከተሰጠው ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ሙሉ በሙሉ መታገዱን የሚያሳውቅ ደብዳቤ እንዲደረሰው መደረጉ እንዳስገረመው መግለጹ አይዘነጋም።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here