ሀሙስ መስከረም 09 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዋርዴር ከተማ በአንድ መስጂድ ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የአገር ሽማግሌ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ.ም. በምሥራቃዊ የክልሉ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ዶሎ ዞን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ፤ በአካባቢው ባሉ ጎሳዎች መካከል ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረ ግጭት ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ተነግሯል።
አቂል ሞሐመድ ሞሐሙድ የተባሉት የአካባቢው የአገር ሽማግሌ ጥቃቱ መፈጸሙን እና ወጣቶቹ መገደላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
የተገደሉት ወጣቶች የሃይማኖት ተማሪዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌው “በስድስቱ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ ዘግናኝ ነው” በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ የተገደሉት ኩጂር በተባለው መስጂድ ውስጥ ለሶላት እየተዘጋጁ ሳለ መሆኑን የገለጹት የአገር ሽማግሌው፤ “ታጣቂዎቹ በአነስ ባለ መኪና ወደ መስጂዱ መጥተው በልጆቹ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል” ብለዋል



