አርብ መስከረም 17 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ለተሽከርካሪ ቦሎ፣ ስም ዝውውር እና የጠፋ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት እስከ 150 ፐርሰንት የሚደርስ የክፍያ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።
የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ያወጣው ይህ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ በተቋሙ ታሪክ ከፍተኛው ነው።
የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በአራት ቀን በፊት በቂርቆስ ክፍል ከተማ እንደ ሞዴል ተደርጎ የታሪፍ ክፍያውን ማስከፈል ያስጀመረ ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።
በዚህም መሰረት ለቦሎ የነበረ ክፍያ ከ650 ብር ወደ 1,850 ብር ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን፣ ለስም ዝውውር ከ5,600 ብር የነበረው ወደ 10,000 ብር፣ ለለተሽከርካሪ የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ 17ሺህ 100 ብር የነበረው ወደ 30 ሺህ ፣ የጠፋ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት 750 ብር የነበረው ወደ 5 ሺህ ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አዲስ ማለዳ አሰምታለች።



