👉አመራሩ በኦሮሚያ የቀቀጠለውን ግጭት ለማስቆም ከመንግስት ንግግር ሊያደርጉ እንደሚችሉም ፍንጭ ሰጥተዋል
ቅዳሜ መስከረም 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሳችንን አግልለናል ሲሉ የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኝ ነጋሳ አስታውቀዋል።
ጃል ሰኝ ነጋሳ መሆናቸውን ያስተዋወቁት የድርጅቱ አመራር፣ ከተመረጡ መገናኛ ብዙሀን ዘጋቢዎች በስልክ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የት እንደሆኑ ባልተገለፀ ቦታ ሆነው በሰጡት ምላሽ፣ ረቡዕ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ/ም የወጣውና የማዕከላዊ ዞን ዕዝ፣ በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው ቡድን መለየቱን የሚገልፀው መግለጫ፣ የእሳቸውና የቡድናቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ጃል ሰኝ ተለይተው የወጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ ” ህግና ደንብ የሌለበት እንዲሁም መተዳደሪያ ደንብ የሌለው ድርጅት ነው፣ ጥፋት ሲሰራም ተጠያቂነት የሌለበት ድርጀት ነው፤ በአንደ ሰው የሚመራ መሆኑን አይተንና ተረድተን ወደ ድርጀቱ ደንብና ህግ ተመልሰን እርስ በርሳችን እናሰተካክል ብለን ነው የምንቀሳቀሰው” ብለዋል።
በኦሮሚያ የቀጠለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ነን ሲሉም ጃል ሰኝ መሰከረም 16 ቀን 2017 በሰጡት በዚሁ መግለጫ ተናግረዋል።



