እሁድ መስከረም 19 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች አመራሮች ከደቡብ ምስራቅ ዞን የተወከሉ ነዋሪዎች ጋር በሰማዕታት ሃውልት ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ የውይይት መድረክ “የትግራይ ህዝብ ከቁጥር በላይ ተአምር እንዲሰራ ያደረጋቸው አንድነታቸው ነው።” ሲሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም “በህዝባዊ ኮንፈረንሱ ላይ የሚሳተፉት ሰዎች ከድጋፍ በላይ ጥያቄዎች ስላሏቸው ትልቅ ኃላፊነት ይሰጠናል” ብለዋል።
“በህወሓትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ምንም ዓይነት ጠብ የለም” ያሉት አቶ ጌታቸው “በፓርቲያችን አመራር መካከል ያለው አለመግባባት ከኛ ጋር ይኖራል እንጂ ወደ ህዝብ አይወርድም” ብለዋል።
አቶ ጌታቸው “በፀጥታ ሃይሎች ላይ የሚደርሰው ስም ማጥፋት እውነት አይደለም።” ስለማለታቸው አዲስ ማለዳ ሰምታለች።



