በ50ኛው የበርሊን ማራቶን  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፃታዎች አሸናፊ መሆን ችለዋል

0
280

እሁድ መስከረም 19 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደምቀው ታይተዋል።

በወንዶች ውድድር ሚልኬሳ መንገሻ በ2:03:17 በመጨረስ አሸናፊ መሆን ችሏል። የ24 አመቱ አትሌት ኬንያዊውን ሲብሪያን ኮቱት በ5 ሰከንዶች በመቅደም ነው አሸናፊ መሆን የቻለው።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሀይማኖት አለው በ2:03:31 ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

በሴቶች ውድድር ደግሞ ትዕግስት ከተማ በ2:16:42 አሸናፊ መሆን ችላለች።

ባለፈው የውድድር አመት ትዕግስት አሰፋ የማራቶንን ክብረ ወሰን በዚሁ ውድድር ማሽሻሏ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ደግሞ የልምምድ ጏደኛዋ ድል ማድረግ ችላለች።

የ26 አመቷ አትሌት ባለፈው ጥር ወር የመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯን በዱባይ አድርጋለች። ከመሃል ርቀት ውድድር የተገኘችው አትሌት ይህንን ውድድር በፍፁም የበላይነት አሸንፋለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት መስታወት ፍቅር በ2:18:48 በሁለት ደቂቃ በመግባት በሁለተኝነት ጨርሳለች።

ቦሰና ሙላቴ ደግሞ በ2:19:00 በመግባት ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ በመያዝ ድል አድርገዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here