እመቤት መለሰ ( ዶ/ር) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነዉ ተሾሙ!

0
520

ረቡዕ መስከረም 22 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)በቅርቡ የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመው የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር መስከረም 20 ቀን 2017 በፃፈዉ ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው ዶ/ር እመቤት ከጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን አሳውቀዋል።

እመቤት የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸውም በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስትራቴጂ ፕላኒንግና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል።

የፓሊሲ ባንኩን ላለፉት 4 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት ዮሐንስ አያሌው በግል ምክንያት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ካስታወቁ በኃላ የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በቅርቡ መሾማቸው ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here