ቅዳሜ ታህሳስ 3 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ በሁሉም ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔ አሳልፏል።።
ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከልም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በተጨማሪም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ እንዲሁም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ተወስኗል።



