የአውሮፓ ህብረት የውጪ ግንኙነት እና የደህንነት ፖሊስ ጉዳዮች ተወካይ እና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ቦሬል ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ምክክር በነሐሴ ወር ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ህብረቱ ታዛቢዎቹን እንደሚልክ ይፋ አደረጉ።
ጆሴፍ በትዊተር ገፃቸው ይፋ እንዳደረጉትም መጪው ምርጫ ለኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዴሞክራሲን ለማምጣት ወሳኝ መለኪያ እደሆነ ገልፀው ህብረቱ ለዐቢይ አህመድ የለውጥ አጀንዳ ያለውን ድጋፍ ያረጋገጠበት ምክክር እንደነበርም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ በተመሰሳይ በግል የትዊተር ገፃቸው ላይ ይፋ እንዳደረጉት ከምክትል ፕሬዘዳንቱ ጋር ‹‹ኢትዮጵያ ስለጀመረችው የብልፅግና ጉዞ እና በቀጠናው ስላሉ መሻሻሎች መክረናል›› ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ያካሄደቻቸውን አገር አቀፍ ምርጫዎች በተደጋጋሚ መታዘቡ ይታወሳል።



