የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከኮሮና ስጋት ጋር በተያያዘ ከመጋቢት 10 እስከ 24 ድረስ በከፊል እንደሚዘጉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መአዛ አሸናፊ ገለፁ።
በከፊል ለመዝጋት የታሰበውም ማሕበራዊ ቅርርብን ለመቀነስ እንደሆነም ፕሬዝዳንቷ ዛሬ መጋቢት 09/2012 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።
ፍርድ ቤት ቀጠሮ ያላቸው ሰዎች ቀጠሯቸው መች እንደሆነ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ይላክላቸዋል ብለዋል።



