በኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት የሚያግዝ ዲጂታል የጦር መሣሪያ መመዝገቢያና መቆጣጠሪያ መተግበሪያ መዘጋጀቱን የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአፍሪካ ደረጃ የሚከበረው ‘አፍሪካ አምነስቲ ወር’ የተሰኘው ከሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር የፀዳ ወር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረ ሲሆን ይህንኑ በማስመልከትም የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅን የተመለከተ ጉባዔ ተካሂዷል።
በጉባዔው የጦር መሣሪያ መመዝገቢያና መቆጣጠሪያ መተግበሪያው በ2012 የወጣውን ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም እንደሚያግዝ የሠላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል “ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በአፍሪካ ሠላምና ደህንነት ላይ ግጭትና ስጋት በመፍጠር ሕዝቡን ለከፋ ጉዳት እየዳረገ ነው” ብለዋል።
ዘገባው የኢዜአ ነው።



