ደንበኞች እየተጠቀሙበት የሚገኘው የሞባይል አገልግሎት ቁጥር (ሲም ካርድ) በስማቸው የተመዘገበ መሆን አለበት ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አሳሰበ።
ጥቂት የማይበሉ የሞባይል አገልግሎት ደንበኞቹ እየጠቀሙበት የሚገኘው ሲም ካርድ በመስማቸው ያልተመዘገ በመሆኑ ሞባይላቸው በሚጠፋበት ጊዜ ምትክ ሲም ካርድ ለማግኘት፣አገልግሎታቸው በተለያዩ ምክንያት ሲቋረጥ መልሶ ለማስቀጠል ደንቦኞች ወደ ሽያጭ ማዕከላቱ ቢቀርቡም ጥያቄውን ለማስተናገድ እንደተቸገረም ኩባንያው አስታውቋል።
ይሁን እንጂ በስማቸው ያልተመዘገበ ሲምካርድ እየተጠቀሙ ያሉ ደንበኞች የስም ዝውውር ለውጥ ማድረግ የሚቻልበትን አሠራር ተግባራዊ ማድረጉን ኢትዮቴሌኮም ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ አስታውቋል።
በዚሁ መሰረትም ደንበኞቹ ቀደም ሲል አገልግሎት በስማቸው ካስመዘገቡት ደንበኛ ጋር በአካል በቅርብ መገኘት የማይችሉ ከሆነ ለዚሁ ዓለማ የተዘጋጀውን ቅጽ (ውል) በመሙላት የስም ዝውውሩን በቀላሉ ማከናወን የሚችሉ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩልም በስማቸው የተመዘገበውን ሲምካርድ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ በሚፈልጉበት ጊዜ በኩባንያው የሽያጭ ማዕከል በመቅረብ ዝውውሩን በሕጋዊ መንገድ እንዲፈጽሙ እና ራሳቸውን ከቴሌኮም ማጭበርበር እንዲጠብቁ ኢትዮ ቴሌኮም አሳስቧል።



