በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የፋይናንስ እና የቴክኒካል ድጋፍ ለማግኘት ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን በዚህ መሰረት የኤሌክትሪክ አውቶብስ በከተማው ላይ የሙከራ ትግበራ ለማከናወን ተቀማጭነቱ እንግሊዝ አገር ካደረገው C40 Cities ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል።
ቢሮው ከC40 Cities ጋር በመተባበርም የኤለክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ በከተማ ፈጣን አውቶብስ (BRT) ኮሪደር ላይ እንዴት እንደሚተገበር በተመለከተ አለማቀፋዊ የኹለት ቀናት ቨርቹዋል አውደ ጥናት ማካሄዱም ለማወቅ ተችሏል።
የከተማ ፈጣን አውቶብስ (BRT) የሚጠቀምባቸውን በናፍጣ የሚሰሩ እና ሌሎቹን አዉቶቡሶች በቀጣይ ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር እቅድ እንደተያዘም ተነግሯል፡፡



