በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እያቀረበ ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ድጋፍ ለማስቀጠል 170 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በፍጥነት ያስፈልገኝል አለ።
ገንዘቡ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ለማድረስ እንደሚውል በፍጥነት ያስፈልገኛል ሲል አዲስ አበባ ባለው የድርጅቱ ቢሮ በኩል አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እስከ እዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ 4.5 የሚሆኑ በትግራይ ክልል ለሚኖሩ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ አቅርቦት እንደ ሚያስፈልጋቸው እና ከዚህም ውስጥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም 1 ነጥብ አራት ሚሊየን ለሚሆኑት ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ድጋፍ እዲሸፍን ጥሪ ማድረጉን ገልጿል።
ባለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ እና ወቅቱ ሰብል የሚሰበሰብበት ጊዜ በመሆኑ በክልሉ የተመረተውን ሰብል መሰብሰብ ባለመቻሉ እና እሱን ተከትሎ የገበያ ስርአቱ በመዛባቱ የተነሳ የተረጂዎችን ቁጥር እንዲጨምር የራሱ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ግጭቱን ተከትሎ በክልሉ ያሉት እንቅስቃሴዎች መስተጓጎላቸው በቂ ምርት ወደ ክልሉ እየገባ ባለመሆኑ ፣ ጥሬ ገንዘብ ቢኖራቸው እንኳን የምግብ ሸቀጻ ሸቀጦች ዋጋ እጅግ በመናሩ የተነሳ በክልሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንዳባባሰው ድርጅቱ በመግለጫው አስታውቋል።
“ የድርጅቱ ካንትሪ ዳይሬክተር ስቲቨን ኦማሞ በምሥራቃዊ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምእራብ ትግራይ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ እንዳሉት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ከሚሹ አካባቢውን ነዋሪዎች በተጨማሪ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የመጡ ዜጎችን ማገዝ ተጨማሪ ስራ የሚጠይቅ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።
“የትግራይ ህዝብ ፅናትን አድንቀው የህዝቡንም ችግርን የመቋቋም አቅም በእውነቱ ያልተለመደ በማለት ገልጸው ነው፣ መንግሥት እና አጋሮች ለብዙዎች ሕይወት አድን ምግብና የተመጣጠነ ድጋፍ እየሰጡ ቢሆንም ፣ለእነዚህ ተጋላጭ ሰዎች የምግብና የተመጣጠነ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ብዙ ተጨማሪ ነገሮች ያስፈልጋሉ ።”በማለት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
“ሁኔታው በጣም ፈታኝ ቢሆንም የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ሰፊው የክልሉ አካባቢዎች ሊደርስ እንደሚችል መገንዘብ አስፈላጊ ነው” ብለዋል ።
“አሁን ግን የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በፍጥነት እና ሙሉ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም የላቸውም ስለሆነም በመላው ትግራይ ህይወትን እና ኑሮን ለመታደግ የተባበረ ጥረታችንን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲደግፍ እናሳስባለን ።ምንም ጊዜ ልናጠፋ አይገባም ብለዋል።”
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ የአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ከማቅረብ በተጨማሪ በሚቀጥሉት ስድስት ወራቶች እስከ 875,000 ተጋላጭ ነፍሰ ጡር ወይም ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች እንዲሁም በክልሉ ለሚገኙ ሕፃናት የምግብ ድጋፍ መስጠት መጀመሩን ተናግሯል ።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በተጨማሪም ለመንግስት እና ለአጋር አካላት የትግራይን እና የክልሉን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል። በተጨማሪም በትግራይ በአዲ ሃሩሽ እና ማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ ለሚኖሩ 35,000 ኤርትራዊያን ስደተኞች ወርሃዊ የምግብ ድጋፍ እየሰጠ እነደሚገኝም ገልጿል።
ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013



