ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ሰመራ ገቡ

0
919

ዕረቡ የካቲት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ገብተዋል።

ኦባሳንጆ ሰመራ ሲገቡ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በሰመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሀንፈሬ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዩ መልእክተኛው ከትናንት በስተያ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው በህወሃት ብድን ጉዳት የደረሰባቸውን፣ የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅን እና ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታልን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here