ረቡዕ የካቲት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሀመድ የአፋር ክልል ርዕሰ ከተማ ሰመራ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቷና ምክትል ዋና ጸሃፊዋ ሰመራ ከተማ ሲደርሱ፤ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





