አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ

0
529

ዕረቡ የካቲት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት እስከ የለሊት አገልግሎትን ለመስጠት ተገልጋዮች የሚበዙባቸውን የአዲስ አበባ አካባቢዎች የመለየት ሥራ እያከናወነ ሲሆን፤ ጥናቱ ሲጠናቀቅ እስከ ምሽት 3 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡት አውቶብሶች እስከ ለሊት 6 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ወደ ሥራ እንደሚያስገባ አስታውቋል።

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምስክር ማንደፍሮ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደገለፁት ፥ “አሁን እስከ 3 ሰዓት ብቻ ነው አገልግሎት የሚሰጡት ከዚህ በኃላ በምንጀምረው አዲስ አገልግሎት እስከ ለሊት አጋማሽ ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የትኞቹ መስመሮች ለእንደዚህ አይነት ሥራ ተጋላጭ ናቸው / የትኞቹ መስመሮች አምሽተው የሚሰሩ በዛ በምናስበው ሰዓት ከስራቸው የሚወጡ ማህበረሰቦች አሉ የሚለውን ጥናት እያደረግን ነው፤ ጥናቱን ከጨረስን በኃላ የተወሰኑ እንደ ዲሞንስትሬሽን የምንጀምረው አሰራር ይኖራል” ብለዋል።

አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት የቀኑን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት የአዲስ አበባ አስተዳደር ይገዛቸዋል የተባሉትን 3 ሺህ አውቶብሶች እየጠበቀ እንደሚገኝ እና አውቶብሶቹን እንደተረከበ በመጠኑ ችግሩን ለማቃለል እንሞክራለን ሲል አሳውቋል።

አሁን ላይ አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት 630 አውቶብሶች ያሉት ሲሆን በ125 መስመሮች በቀን ውስጥ እስከ 600 ሺ ያህል ሰዎችን እንደሚያጓጉዝ ገልጿል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here