በአማራ ክልል ከ45 ሺሕ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

0
498

የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ፣ የአማራ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ‹ሆፕ ፎር ጀስቲስ› ለ5 ዓመት የሚቆይ የጎዳና ተዳዳሪዎችንና ወላጆቻቸውን ለማቋቋም 154 ሚሊዮን 685 ሺሕ ብር በላይ ሥምምነት መፈራረማቸው ተሠምቷል።
በተለይ በአሁኑ ወቅት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የትግራይ ቡድን ባካሄደው ወረራ ምክንያት በክልሉ በርካታ የተቸገሩ ሕፃናትና ሴቶች በመኖራቸው ረጅ ድርጅቶች ጉልህ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል ተብሏል።
ድርጅቱ በሚቀጥሉት 5 ዓመት በአማራ ክልል መኖሪያቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ሕፃናት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀልና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ በማቀዱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ከድርጅቱ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ አብራርተዋል።
ድርጅቱ በባህር ዳር ከተማ በዓመት 200 ሕፃናትን ከጎዳና ላይ በማንሳት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለማቀላቀል ማቀዱም ነው የተገለጸው። ይህም ሕፃናትን ማቋቋም ብቻ ሳይሆን ሊደርስባቸው የሚችለውን የሥነ-ልቦና ጉዳት እንደሚጠግኑም ይረዳል ተብሏል።
ድርጅቱ በአገር አቀፍ ደረጃ 6 የሕፃናት ማቆያ እንዳለውና
የአምስት ዓመታት ዕቅዱን ለማሳካት 154 ሚሊዮን 685 ሺሕ ብር በላይ በጀት መድቦ፣ 45 ሺህ ተጠቃሚዎችን ተደራሽ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።
ሆፕ ፎር ጀስቲስ በጎዳና ላይ የሚኖሩትን ሕፃናት በመታደግ ዘላቂ ሕይወትን እንዲኖሩ ጥረት እንደሚያደርግ ነው የተመላከተው።
ድርጅቱ በሚያደርገው የአምስት ዓመታት ቆይታ፣ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ የሚያደርጉ ዜጎችን ለመታደግ ተጨባጭ ተግባራትን መሥራት እንደሚጠበቅበትም ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ሐሳብ እንደቀረበለት ተነግሯል።
ሆፕ ፎር ጀስቲስ ባለፉት 3 ዓመታት በአማራ ክልል 7 ሺህ 500 ተጠቃሚዎችን ተደራሽ ማድረጉ ይነገራል።


ቅጽ 4 ቁጥር 171 የካቲት 5 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here