በሱሉልታ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት 20 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና 400 የክላሽንኮቭ ጥይት ተያዘ

0
725

ሐሙስ የካቲት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት 20 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና 400 የክላሽንኮቭ ጥይት መያዙን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትልና ጥቆማ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪው እጅ ከፍንጅ ሊውል ችሏል።

ከህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ በተጠረጠረ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የካቲት 15 ቀን 2014 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በተደረገ ፍተሻ ነው የጦር መሳሪያው ሊያዝ የቻለው።

ከ20 ቱርክ ስራሽ ሽጉጡቹ ጋር ከ8 መሰል ጥይት የተያዘ ሲሆን 400 የክላሽንኮቭ ጥይትም አብሮ የተገኘ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ጠቁሟል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here