ማክሰኞ የካቲት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሱሉልታ ከተማ በተደረገው የሕገወጥ ንግድ ቁጥጥር በሕገወጥ መንገድ የተከማቸ 20,000 ሊትር የምግብ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ።
የከተማው የገበያ መረጋጋት ኮሚቴ በአራት የንግድ ቤቶች ውስጥ ባደረገው ፍተሻ ነው 20 ሺህ ሊትር ዘይት በቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡
በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘይት ከዚህ ቀደም በነበረው የገበያ ዋጋ ለነዋሪዎች እንዲሸጥ መደረጉን ከኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





