የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ

0
758

ዕረቡ መጋቢት 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተገለፀ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች ነግረውኛል ሲል ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ተወልደ ገ/ማርያም አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 ዓመታትም አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here