አርብ መጋቢት 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከማለዳው ጀምሮ በተደረጉ ሦስት በረራዎች በጠቅላላው 1 ሺህ 173 ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተረገ ያለው ጥረት ቀጥሎ ዛሬ በጅዳ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ተጀምሯል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአጠቃላይም ከዕሮብ ጀምሮ ከስኡዲ አረቢያ 2 ሺህ 111 ዜጎችን ማስመለስ መቻሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n






