ኢትዮ ቴሌኮም ከአማራ ባንክ ጋር ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ

0
580

ማክሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል ገንብቶ አገልግሎት ላይ ያዋለ ሲሆን፤ ይህንኑ ከፍተኛ አቅም ያለውን የመረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ሥምምነት ከአማራ ባንክ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡፡

ይህም የባንኩን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓት በዚህ እጅግ ዘመናዊ እና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ የመረጃ ማዕከል አማካኝነት አስተማማኝ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት ያስችለዋል ተብሏል፡፡

ሥምምነቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የአማራ ባንክ ፕሬዝዳንት ሔኖክ ከበደ ተፈራርመዋል።

ይህ ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል ከፍተኛ የራሱ መጠባበቂያ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ያለው፣ እጅግ ጠቀሜታ ያለውን የዳታ አገልግሎት ማስቀመጥ በሚያስችል መልኩ ዲዛይን የተደረገና በሰለጠነ የሰው ኃይል የሚመራ ከፍተኛ አቅም ያለው የዳታ ማዕከል ነው መባሉን ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል።

በተጨማሪም፤ የሞጁላር የመረጃ ማዕከሉ አገልግሎት እንዳይስተጓጎል የሚያስችል 99 በመቶ አስተማማኝ የኔትዎርክ አቅም እንዲኖረው ከአምስት በላይ አቅጣጫዎች በአውቶማቲክ ማዞሪያ በሚሰራ የፋይበር ኮኔክሽን የተገጠሙለት ሲሆን፤ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በማዕከሉ ውስጥ ያሉ ሲስተሞች ላይ የኔትዎርክ ኮኔክሽንም ይሁን ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች ቢያጋጥሙ ፈጣን ፍተሻና ጥገና ለማከናወን የሚያስችል ሥርዓት ያለው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የመረጃ ማዕከል ነውም ተብሏል፡፡

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here