በ10 ዓመቱ የቤት ልማት መሪ ዕቅድ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ቤቶች ይገነባሉ ተባለ

0
933

ማክሰኞ ሚያዚያ 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በ10 ዓመቱ የቤት ልማት መሪ ዕቅድ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን የከተማ ቤቶች ለመገንባት ማቀዱን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከዚህ ባለፈም በገጠር የቤት ልማት ንዑስ ፕሮግራም 2 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚደርሱ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ መያዙ ተመላክቷል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለማሸጋገር በዛሬው ዕለት አገር አቀፍ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በሥራ ላይ የነበሩት የከተማ ቤት አቅርቦት የስትራቴጂ ማዕቀፍና የገጠር ቤት ልማት ስትራቴጂን በማሻሻል የግል ሴክተሩን ተሳትፎ ለማሳደግ መሰራቱን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ ከተሞች ተደራሽና ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤቶችን በፍጥነት፣ በጥራትና በብዛት ለማቅረብ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ባለፈ ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማጎልበት ብሎም ያረጁና የተፋፈጉ የከተማ አካባቢዎችን ለማደስ አዲሱ ሴትራቴጂ ይግዛል ነው ያሉት፡፡

ካለፉት ዓመታት የልማት ውጤቶችና ልምድ በመነሳት በአገሪቱ በመኖሪያ ቤት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ በማድረግ በቤት ልማት ዘርፍ የግል ሴክተሩ የአንበሳውን ድርሻ እንዲወስድ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ በሚቀጥሉት አስር ዓመታትም በከተሞች ለመገንባታ ከተያዘው 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ቤት ውስጥ የግል ሴክተሩ 80 በመቶውን ይሸፍናል።

ከእቅዱ ጋር ተያይዞም በመካከለኛ እና ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት የሚያስችሉ አቅሞችና ዕድሎችን በሚገባ በመፈተሽ፣ የአቅርቦት ችግርን ለመፍታት እየሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

የሪል ስቴት ዘርፉ ተገቢው የህግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅለት በማድረግ እያደገ የሚሄደውን የቤት ፍላጎት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማስተናገድና የሪል ስቴት አልሚዎች በተገቢው መንገድ እንዲደራጁ የመንግስትን ድጋፍ መጠቀም እንዲችሉ እንደሚያግዝም ተመላክቷል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here