በመዲናዋ በአንድ የእንጨት ሥራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺህ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ

0
1270

ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ባደረጉት ክትትል በአንድ የእንጨት ሥራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺህ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ኹለቱ ተቋማት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ቀለበት መንገድ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ሥራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ጥይት ስለመኖሩ ከህዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ፤ ሲከታተሉ ቆይተው ግንቦት 8 ቀን 2014 በህግ አግባብ በድርጅቱ ውስጥ ባደረጉት ብርበራ በ4 ማዳበሪያ ተጠቅልሎ በድብቅ የተቀመጠ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ሊያስከትል የሚችለውን አገራዊ ጉዳት ተገንዝቦ የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተሳታፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰጠ ያለውን ጥቆማ እና መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here