ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የመንግስትን መሬት ለግል ጥቅማቸው በማዋል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ

0
924

ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የመንግሰትን መሬት ለግል ጥቅማቸው በማዋል የተጠረጠሩ ሦሶት ግለሰቦችን በእስራት እና በገንዘብ መቅጣቱን የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ 1ኛ ፉንጊቻ ዴንጌ፣ 2ኛ አብዱልአዚዝ አሊ፣3ኛ ሁሴን አሊዮ የተባሉ ሲሆኑ፤ በሞያሌ ከተማ ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በማለት ፍርድ ቤቱ ከ7 ዓመት እስከ ስምንት ወር የሚደርስ ፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣት በይኖባቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ፍረድ ቤቱ አንደኛ ተከሳሽ የሞያሌ ከተማ ከንቲባ የነበሩ ፉንጊቻ ዴንጌን እና ኹለተኛ ተከሳሽ አብዱልአዚዝ አሊን በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺህ ብር መቀጮ እንዲሁም ሦስተኛ ተከሳሽ ሁሴን አሊዮን በ8 ወራት ቀላል እስራት እና በ1 ሺህ ብር ቅጣት መበየኑን ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here