ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆነት ኮለሬል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ የፌደራልጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ።
ኮለሬል ገመቹ አያና በግንቦት 9 ቀን 2014 በተከሰሱበት በሽብር ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና የህገመንግክት ጉዳዮች ወንጀል ችሎች በነጻ ከተሰናበተ በኋላ፤ በነጋታው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው ለ6 ወር በገላን ፓሊስ ጣቢያና በወታደራዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ እርባታ ውስጥ ታሶሮ እንደነበርና ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በእስር ላይ እንደነበሩ ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።
በኮለሬል ገመቹ አያናን በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል የምርመራ መዝገብ እኖዳልተከፈተበት የፌደራል ፖሊስ ቀርቦ ማብራሪያ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።
ሰበር ሰሚ ችሎቱ የኦሮሚያ ፖሊስ ቀርቦ በኮለሬል ገመቹ የእስራት ሁኔታን እንዲያስረዳ ታዞ በትናንትናው የችሎት ቀጠሮ አለመቅረቡን ተከትሎ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለዛሬ በይደር ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፤ መርምሮ ኮለሬል ገመቹ አያና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።




