ዕረቡ ግንቦት 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጠላቶችን ቅስም የሰበረ መሆኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በመግለጫቸውም የአማራ ክልል ሕግ የማስከበር ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
የውስጥ ሥርዓት አልበኝነትን የማስቆም ሥራ የወገንን ኃይል ያጠናከረ የጠላትን ኃይል ቅስም የሰበረ ነው ብለዋል።
የሕግ ማስከበሩ ተግባር ሕገወጥነትንና ሥርዓት አልበኝነትን መልክ የማስያዝ ተግባር መሆኑንም መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
የሕግ ማስከበር ሥራው ለውጭ ጠላት ከሚደረገው ዝግጅት አንዱና ዋነኛው ተግባር እንደሆነም አስገንዝበዋል።



