የሙያና ቴክኒክ ባለሙያዎችን ከአሠሪዎች ጋር የሚያገናኝ ድርጅት ሥራ ጀመረ

0
1218

የሙያና ቴክኒክ ባለሙያዎችን ከአሠሪዎች ጋር የሚያገናኝ “ምን ልታዘዝ አዲስ” የተሰኘ አገልግሎት ሰጭና አገልግሎት ፈላጊዎችን የሚያገናኝ ድርጅት ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

“ምን ልታዘዝ አዲስ” ከ30 በላይ የሙያና አገልግሎት ሰጪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ አገልግሎት ፈላጊዎች የሚፈልጉትን ባለሙያ በሞባይል መተግበሪያ፣ በስልክ ጥሪና በድረ ገጽ ማዘዝ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ደንበኞች የሚፈልጉትን ባለሙያ ወይም አገልግሎት ሲያዙ በአቅራቢያቸው ያለውን ባለሙያ እንደሚያቀርብ ድርጅቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የጂብሰም ሥራ፣ የግንበኛ፣ የቀለም ቅብ፣ የልስን ሥራ፣ የኔትወርኪንግ ሥራ፣ የድግስ እቃ ኪራይ፣ የአናጢ ሥራ፣ የሽንትና ቤትና ፍሳሽ አስወጋጅ፣ የተለያዩ የጥገና ሥራ ባለሙያዎችን ከደንበኞች ጋር ያገናኛል ተብሏል።

በቴክኒክ እና ሙያ የሠለጠኑ ዜጎች በይበልጥ የዚህ እድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ድርጅቱ ያስታወቀ ሲሆን፤ በሙያና ቴክኒክ የሠለጠኑ ወጣቶች ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡ ከተለያዩ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር እየሠራሁም ነው ብሏል።

በተለያዩ የሙያ መስኮች ሥልጠና ወስደው የሥራ እድል ላላገኙ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ያስታወቀው ድርጅቱ፣ በዘርፉ ላይ ያለው ክፍተት በጥናት አረጋግጦ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 189 ሰኔ 11 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here