መከላከያ ሚኒስቴር ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የክብር ኒሻን እና የእውቅና ሽልማት አበረከተ

0
1250

ሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ኡንዴ የክብር ኒሻን እና የእውቅና ሽልማት አበርክቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን በአፋር ክልል በኩል በመግባት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያደረገውን ሙከራ፤ የአፋር ክልል ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያ፣ ህዝባዊ ሰራዊትና አጠቃላይ የአፋር ህዝብን በማስተባበር ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር እውቅና በመስጠት ነው የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የክብር ኒሻን ያበረከተላቸው።

ህወሃት በአፉር ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን በመውረርና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ንፁሀን አርብቶ አደሮችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል እንዲሁም የህዝብና የግለሰብ ንብረቶችን በማውደም እና በመዝረፍ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ማድረሱ ይታወቃል።

የአፋር ህዝብም ከክልሉ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያና ህዝባዊ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት ታላቅ ድልን ማስመዝገብ መቻሉን ነው የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ የገለፀው።

ለዚህም ብርቱ የጀግንነት ተግባር የአገር መከላከያ ሰራዊት እውቅና መስጠቱ ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here