ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስተዳደሩ በሰጠው መግለጫ እንደገለፀው፣ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር እንደማቻል ነው።
የከተማ አስተዳደሩ በየሦስት ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው የተነገረ ሲሆን፣ በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩና በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉ ተነግሯል።
በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ ዐይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም ዓይነት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም መባሉ ተዘግቧል።
አከራዮችም ሆኑ ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሠሩም የተነገረ ሲሆን፣ መቼ እንደሚሻሻልም ሆነ ውሳኔ እንደሚያገኝ የተነገረ ነገር የለም።
ቅጽ 4 ቁጥር 192 ሐምሌ 2 2014


