ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በዓለም አቀፉ የአካባቢ፣ ማህበራዊና የአስተዳደር ፎረም በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ

0
1002

ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዲሪ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ኮሪያ, ሲዎል ከዛሬ ነሐሴ 23 እስከ 25 ቀን 2014 ድረስ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ ማህበራዊና የአስተዳደር ፎረም ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ኮሪያ ተገኝተዋል።

ሚንስትሩ በአብይ ጉባኤው መድረክ ላይ የአየር ንብርት ለውጥ በኢትዮጵያ እያስከተለ የሚገኘውን አደጋ እንዲሁም እየተወሰደ የሚገኘውን የመፍትሄ አቅጣጫ አስመልክቶ ጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን፤ በቆይታቸው የፕሮጀክት ትብብር ሥምምነቶችን ከኮሪያ የውኃ ኮርፖሬሽንና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ይፈራረማሉ ተብሎ ያጠበቃል።

ሚኒስተርሩ ፎረሙ በይፋ ከከፈቱት ከቀድሞ የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን ጋር ተገናኝተው በአካባቢ ጥበቃና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የተነጋገሩ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ከተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዳይሬክተር ጃሚል አህመድ ጋር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምና አካባቢ ጥበቃ ሥራ መወያየታቸውን ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ከዚህ በፊት ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ሰኔ 6 ቀን 2014 የደቡብ ኮሪያን የውኃ ኮርፖሬሽን የአውሮፓና የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ሺን ኪንግሺንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በኹለትዮሽ የትብብር ዕድሎች ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here