የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ጥብቅ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

0
1205

ማክሰኞ ነሐሴ 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማዋ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ በቀጣዮቹ ነጥቦች ላይ ጥብቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት:-

1ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታ በማናፈስ በህብረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር በሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።

2ኛ. በከተማ ደረጃ አገልግሎት የምትሰጡ ታክሲዎች እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።

3ኛ. ወቅታዊ ኹኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።

4ኛ. ከወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በምግብ ቤቶች፣ በመጠጥ ቤቶች፣ በካፌዎችና በግሮሰሪዎች ላይ ከቀኑ 11:00 ሰዓት በኋላ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት የተከለከለ ነው።

5ኛ. የአልጋ አከራይ ሆቴሎዎች የመኖሪያ ቤትና የመደብ አከራዮች፤ የተከራዩን ማንነት የሚገልጽ መረጃ በመያዝ እንድታስገለግሉና በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት የተከራዩን መታወቂያ ኮፒ በማድረግ ጭምር የመሰጠት ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

6ኛ. በከተማው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊቶች፣ ጸጉረ ልውጥ ሰዎች፣ አጠራጣሪ ተሽከርካሪዎች ወዘተ ሲታዩ ለጸጥታ ተቋማት መጠቆም እንደሚገባ ተገልጿል።

7ኛ .በከተማው ውስጥ የሚገኙ DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣ የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

8ኛ .ከዛሬ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ጀምሮ ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ ከቀኑ 11፡ዐዐ ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

9ኛ. በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ሕዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

10ኛ. የከተማዋ የጸጥታ ኃይሎች ከምንግዜውም በላይ በመናበብ በመቀናጀት የተሰጣቸውን ሀላፊነት በብቃት በመወጣት ህግ የማስከበር ሚናቸውን እንዲወጡ በጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። የከተማዋ ነዋሪም በማህበራዊ ማሪያዎች እና በበሬ ወለደ በሀሰተኛ በመለቀቁ መረጃዎች ሳይደናገር እና አላስፈላጊ ውዦብር ውሰጥ ሳይገባ በተረጋጋና በሰከነ መልኩ መደበኛ ሰራውን እንዲያከናውን ተጠይቋል።

11ኛ. ከተፈቀደላቸው የከተማዋ የፀጥታ ኃይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ በቡድንም ሆነ በግል ይዞ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑም ተገልጿል።

12ኛ. መንግስት ከሚሰራቸው የተቀናጀ ድጋፍ አሰባሰብ ሥርዓት ውጭ ለመከላከያ፣ ለልዩ ኃይል ድጋፍ በሚል ሰበብ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ግብዓቶችን ማሰባሰብ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና በግልም ሆነ በቡድን ወደ ግንባር መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።

13ኛ. ማንኛውም ተቋማት ተሽርካሪዎችን ለጸጥታ ሥራ በተፈለጉ ጊዜ የጸጥታ ተቋሙ ሲጠይቅ ቀና ትብብር እንዲያደርጉም የከተማ አስተዳዳሩ አሳስቧል።

ለተጨማሪ መረጃ
0335510005
0335510945
0921038804 ማድረስ እንደሚቻል የገለጸው ከተማ አሥተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት በየጊዜው የሚያወጣቸውን ውሳኔዎች እንደሚያሳውቅም ገልጿል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር
ነሐሴ 24 ቀን 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here