በመዲናዋ የህወሓት ተላላኪ የሆነ ግለሰብ ራሱን ደብቆ ቄስ በመምሰል የእምነት መፅሐፍ ይዞ ሲንቀሳቀስ በፀጥታ ሃይሎች ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

0
1018

ዕረቡ መስከረም 11 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የህወሓት ቡድን ተላላኪ የሆነ ግለሰብ ራሱን ደብቆ ቄስ በመምሰል የእምነት መፅሐፍ ይዞ ሲንቀሳቀስ በፀጥታ ሃይሎች ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል፡፡

ይህ ግለሰብ ራሱን የኦርቶዶክስ ቄስ በማስመሰል እኩይ አላማቸውን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን፤ በሰላም ሰራዊት አባላት ጥርጣሬ ክትትል መነሻ በፀጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጸ/ቤት አስታውቋል፡፡

በተደረገ ማጣራትም ግለሰቡ ምንም አይነት የቅስና ሙያ የሌላውና ራሱን ቀይሮ ለድብቅ አላማው ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑ ታውቋል ተብሏል፡፡

አሁንም ህብረተሰቡ አሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ ቡድኖች የህዝባችንን ሰላም ለማወክ ምንጊዜም ያለእረፍት የሚሰሩ መሆኑን በመረዳት፤ ከፊታችን ያሉ በዓላትም በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ፀጉረ ልውጦችን በትኩረት በመከታተል አካባቢውንና ከተማውን እንዲጠብቅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here