10 በአፍሪካ ብዙ ተናጋሪ ያላቸው ቋንቋዎች

0
2349

ምንጭ፡-ቶክ አፍሪካና (2022)

አፍሪካ በዓለማችን ካሉ አኅጉራት በሕዝብ ብዛት ኹለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ታድያ እንደ ሕዝቧ ብዛት ሁሉ ያሏት ቋንቋዎችም ብዛታቸው ቀላል የሚባል አይደለም። ምንም እንኳ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ውስጥ የወደቁ በመሆኑ የራሳቸውን ቋንቋ በሚገባ ማሳደግ ባይችሉም፣ ብዙ ተናጋሪ ያላቸውና መሠረታቸው እዚሁ አፍሪካ የሆነ ቋንቋዎች አሉ።

በዚህም መሠረት በአፍሪካ በጠቅላላ ሦስት ሺሕ የሚጠጉ ቋንቋዎች እንዳሉ ይነገራል ሲል ቶክ አፍሪካና በገጹ ባስነበበው ጽሑፍ ጠቅሷል። ታድያ በድምሩ ከሚያገለግሉ ቋንቋዎች መካከል ብዙ ተናጋሪ ያለው እንግሊዝኛ ነው። በአንጻሩ አፍሪካዊ የሆነው ስዋሂሊ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 10 በመቶ የሚሆኑ አፍሪካዊያን የስዋሂሊ ተናጋሪ መሆናቸውም ይነገራል። በዝርዝሩ አምስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት፣ ሀውሳ እና ዮርባ የተሰኙ ቋንቋዎች በናይጄሪያ ብሔራዊ ቋንቋ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው።


ቅጽ 4 ቁጥር 204 መስከረም 21 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here