ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር የኹለትዮሽ ውይይት አደረጉ

0
810

ሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሚመራው የኬንያ ሪፐብሊክ ልዑካን ቡድን ጋር የኹለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ኹለቱ መሪዎች መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል::

የኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ በኬንያ በተደረገው አገራዊ ምርጫ ተፎካካሪያቸውን ራይላ ኦዲንጋ በማሸነፍ ስልጣን መያዛቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ዛሬ ማለዳውን ለይፋዊ የስራ ጉብኝ አዲስ አበባ መግባታቸውን ይታወቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here